ደላላ

ከደላሎች ውጪ ሰራተኞችን ከቀጣሪዎች ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ መተግበሪያ ተዘጋጀ

ከደላሎች ውጪ ሰራተኞችን ከቀጣሪዎች ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ መተግበሪያ ተዘጋጀ

የቤት ውስጥ ሰራተኛን ጨምሮ የግል አገልግሎት ሰራተኞች እና አሰሪዎችን የሚያገናኝ፣ ደላላን የሚተካ መተግበሪያ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። የግል አገልግሎት ቅጥር የሚባሉትን እንደ አትክልተኛ፣ የቤት ውስጥ ተንከባካቢ፣ የቤት ውስጥ አብሳይ (ሼፍ) እና ሌሎችም ዘርፎች የቅጥር ግንኙነት ከደላላ ጣልቃ-ገብነት የሚያላቅቅ መተግበሪያ እና አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ እንደሆነ ተገለጸ። ዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት ኮንቬንሽን 189ን ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀው ደንብ ለፍትሕ ሚኒስቴር መቅረቡን እና በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል። አንድ ዓመት አካባቢ ለሚፈጅ ጊዜ ግብዓት በማሰባሰብ እና ባለድርሻ አካላትን በማወያየት የተዘጋጀው ደንብ፣ የቤት ሠራተኞች መመዝገቢያ ሶፍትዌር ሲስተም እንዲኖረው የሚያስችል መተግበሪያ እየተዘጋጀለት እንደሆነ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ…
Read More