Jobsinethiopia

ኢትዮጵያ 50 የኮንስትራክሽን ሰራተኞችን ወደ ጀርመን ልትልክ ነው

ኢትዮጵያ 50 የኮንስትራክሽን ሰራተኞችን ወደ ጀርመን ልትልክ ነው

በኮንስትራክሽን ሥራ የሚሰማሩ 50 ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ወደ ጀርመን ከማቅናታቸው በፊት አዲስ አበባ ባለው የጀርመን ኢንስቲትዩት ተጨማሪ ስልጠናዎችን በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡ በኮንስትራክሽን ሥራ ለመሠማራት የሚያበቃቸውን ሥልጠና ያጠናቀቁ የመጀመሪያው ዙር ባለሙያዎች ወደ ጀርመን እንደሚሄዱ ተገልጿል፡፡ ሥልጠናቸውንና ፈተናቸውን አጠናቀው ጀርመን ከሚገኙ አሠሪዎቻቸው ጋር የሥራ ውል የተፈራረሙት የመጀመሪያዎቹ ተጓዦች በመጪው አንድ ወር ውስጥ  ጉዞ እንደሚያደርጉ ተሰምቷል።  ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በሲቭል ኢንጂነሪንግ፣ በኮንስትራክሽን ማናጅሜንት ቴክኖሎጂ፣ በአርክቴክቸርና መሰል ሙያዎች የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ምሩቃን ወጣቶች ጎኤቴ በመባል በሚታወቀው የጀርመን ባህልና ቋንቋ ኢንስቲትዩት ሥልጠናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ንጉሡ ጥላሁን እንዳሉት ሥልጠናው ከሦሥት ዓመት በፊት በቀድሞው ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር…
Read More