18
Nov
የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል የሶስት ወራት እቅድ አፈጻጸማቸውን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡ ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 140 ሺህ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ ለመላክ ታቅዶ ነበር ብለዋል፡፡ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በዘንድሮ በጀት ዓመት 700 ሺህ ኢትዮጵያውያንን ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ ለመላክ እቅድ እንደነበረውም ሚኒስትሯ አክለዋል፡፡ ተቋሙ በ2016 በጀት ዓመት 332 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ መላካቸውም ተገልጿል። ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች የተላከባቸው ሀገራት ስድስት የመካከለኛው ምስራቅ እና ሁለት የአውሮፓ ሀገራት ናቸው። ሀገራቱ “የሰለጠኑ” እና “በከፊል የሰለጠኑ” ሰራተኞችን ከኢትዮጵያ እንደሚፈልጉ የጠቆሙት ሙፈሪያት፤ በጤና፣ በምህንድስና፣ በአርክቴክቸር፣ በሆቴል እና መስተንግዶ ዘርፎች፣ በኤሌክትሪክ እና ቧንቧ ስራዎች እንደዚሁም…