Silkroadhospital

የሮቦቲክ ሰርጀሪ ህክምና መስጠት የሚያስችል ማሰልጠኛ በአዲስ አበባ ተከፈተ

የሮቦቲክ ሰርጀሪ ህክምና መስጠት የሚያስችል ማሰልጠኛ በአዲስ አበባ ተከፈተ

ማሰልጠኛ ማዕከሉ የተከፈተው በቻይና እና አፍሪካ የህክምና አጋርነት አማካኝነት ሲሆን ዘመናዊ የሮቦቲክስ ሰርጀሪ ህክምናን በኢትዮጵያ እና ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማስፋፋት ያለመእንደሆነ ተገልጿል።​በቻይና እና አፍሪካ ትብብር ለአህጉሪቱ የጤና ዘርፍ ማዘመኛ የሚሆን አዲስ የህክምና አጋርነት ፕሮግራም በአዲስ አበባ ሲልከ ሮድ ጄነራል ሆስፒታል ተመርቋል። ሲልክሮድ ሆስፒታል በቻይናዊያን ከአምስት ዓመት በፊት የተቋቋመ ዘመናዊ ሆስፒታል ነው። ​በዕለቱ የሮቦቲክስ ሰርጀሪ እና የኢንዶስኮፒክ ቴክኖሎጂ ማሰልጠኛ ማዕከላት የተከፈቱ ሲሆን፣ ኘሮግራሙ አነስተኛ ቀዶ ጥገና ቴክኖሎጂን በስፋት ለማስፋፋት ያለመ ነው። ​በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ የዘመናዊ ቴክኖሎጂና የሰለጠነ የሰው ኃይል አስፈላጊነትን ገልጸው፣ የቻይና ባለሙያዎች የሚያደርጉትን የዕውቀትና ክህሎት ሽግግርን አድንቀዋል። ​የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና በኢትዮጵያ የቻይና…
Read More