27
Jul
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ አርሲ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ከ2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ያካሄደውን የምርመራ ግኝት ይፋ ባደረገበት 158ኛ ልዩ መግለጫው፣ ቢያንስ ከ450 በላይ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን አስታውቋል። ሀገር በቀሉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት 37 ገጾች ባሉት ሪፖርቱ መሠረት፣ በዞኑ በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች ውስጥ በታጣቂዎች ማንነትንና ኃይማኖትን መሰረት በማድረግ በተፈጸሙ ጥቃቶች የሰው ህይወት ከማለፉ ባሻገር፣ በርካታ ዜጎች ለአካላዊ ጉዳት፣ ለእገታ እና ለአስገድዶ መሰወር ተዳርገዋል። በተጨማሪም ከ14 ሺህ በላይ ሰዎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፣ በርካታ አብያተ ክርስቲያናትና የግል ንብረቶች መዘረፋቸውንና መውደማቸውን አመልክቷል። ኢሰመጉ ባካሄደው የመስክ ምልከታና መረጃ የማሰባሰብ ስራ፣…