31
Jul
በመካከለኛው ምስራቅ እና በቀይ ባህር ዙሪያ ያለው ጦርነትና ውጥረት ለስራው ፈተና እንደነበር፣ የነዳጅ እጥረትም እንደልብ ለመንቀሳቀስ መቸገርን ጨምሮ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ፈተና እንደነበሩ አስረድቷል። የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ በተመለከተ ዛሬ ከሰዓት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚው ዓመቱ ለዘርፉ ፈታኝና ከባድ ጊዜ ቢሆንም በብዙ መለኪያዎች ግን የተሻለ ሊባል የሚችል ስራ የተሰራበት እንደነበር ጠቁመዋል። በበጀት ዓመቱ ተቋሙ በአጠቃላይ ከ7 ሚሊዮን በላይ ሜትሪክ ቶን ጭነት ማጓጓዝ መቻሉን የተናገሩት ሀላፊው ከዚህ ውስጥ 5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶኑ ከኮንቴይነር ውጪ የሆነ ጭነት፣ 2 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶኑ ደግሞ የኮንቴይነር ጭነት እንደሆነ…