25
Jun
ኢትዮጵያ ከ60 ሺህ ቶን በላይ እቃ የመጫን አቅም ያላትን መርከብ ተረከበች የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በቅርቡ ባህር ዳር እና ሀዋሳ የተሰኙ ሁለት መርከቦች ለኪሳራ ዳርገውኛል በሚል መሸጡ ይታወሳል። በተሸጡት ሁለት መርከቦች ምትክም አባይ የተሰኘች አዲስ መርከብ ከቻይና መግዛቱን አስታውቋል። አዲሷ መርከብም በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት ታሪክ በግዙፍነቷ አቻ የላትም የተባለ ሲሆን መርከቧ በኢትዮጵያ እጅ መግባቷን ድርጅቱ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ድርጅት በ3 ሺህ ቶን የመጫን አቅም ባላቸው መርከቦች ስራውን መጀመሩ ይታወሳል። ኢትዮጵያ የተረከበቻት አባይ የተሰኘችው አዲሷ መርከብ 63 ሺህ 229 ቶን የመጫን አቅም አላት ተብሏል። በቻይናው ያንግዡ ዳያንግ ሺፕ ቢዩልዲንግ የተገነባችው ይህች መርከብ 200 ሜትር ርዝመት እንዳላትም ተገልጿል። ይሁንና…