16
May
የኢትዮጵያ የውጭ እዳ 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ። ኢትዮጵያ ከአገር ውስጥ ባንኮች የተበደረችውን ሳይጨምር ከውጭ አበዳሪ ምንጮች ተበድራ ያልመለሰችው የዕዳ መጠን 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የገንዘብ ሚንስቴር አስታውቋል። እንደ ሚኒስቴሩ ሪፖርት ከሆነ ኢትዮጵያ ካለባት 28 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕዳ ውስጥ 54 በመቶ የተገኘው ከዓለም ባንክና ከአፍሪካ ልማት ባንክ ነው፡፡ 46 በመቶው ደግሞ ከቻይና እና ከሌሎች ውጭ የግል አበዳሪ ተቋማት የተገኘ እንደሆነ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ባለባት ከፍተኛ የውጭ ዕዳ ብድር ምክንያትም በዓለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት ምደባ ከፍተኛ የዕዳ ጫና ያለባቸው አገሮች ዝርዝር ውስጥ ተመድባለች። በተያያዘ ዜና ኢትዮጵያ ከሶስት ዓመት በፊት የቡድን 20 አገሮች የዕዳ ጫናን ለማቅለል ባዘጋጁት የዕዳ መልሶ ማዋቀር ሥርዓት ለመጠቀም…