canada

ኢትዮጵያዊያንን ለስራ ወደ ካናዳ መላክ የሚያስችል ስምምነት ተፈጸመ

ኢትዮጵያዊያንን ለስራ ወደ ካናዳ መላክ የሚያስችል ስምምነት ተፈጸመ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በካናዳ ከሚገኘው ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል (FFI) ጋር በክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራ መስኩ በጋራ መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱ ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች የክህሎት ልማትን ለማጠናከር፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና ዓለም አቀፍ የሥራ ዕድሎችን ለማመቻቸት ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል። በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ ከኢንቨስትመንቶች ሁሉ ትልቁ ኢንቨስትመንት የሰው ኃይል ልማት ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ነው፡፡ ስምምነቱ የሥራ ዕድል ከማመቻቸት ባሻገር ወጣቶችን በስልጠና ማብቃት ላይ ያተኮረ በመሆነ በኢትዮጵያ ወጣቶች ላይ የሚደረግ የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት ነው ብለዋል። ይህም የዜጎችን እምቅ አቅም በመፍጠር ለዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ከማቅረብ ባለፈ አጠቃላይ የሰሪ ኃይላችንን የሚያጠናክር እንደሆነም…
Read More
ካናዳ ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች

ካናዳ ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች

በካናዳ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አማካኝነት የወጣው ይህ ማስጠንቀቂያ ‹‹ወሳኝ ላልሆነ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ወደ ኢትዮጵያ እንዳትሄዱ› የሚል መልእክት ያለው ሲሆን ለዚህም የሰጠው ምክንያት የእርስ በእርስ ግጭት፣ አመፅ፣ የጦር መሳሪያ ግጭት ወንጀል እና የማርበርግ ቫይረስ ስርጭት ናቸው። የጉዞ ማስጠንቀቂያው የፀጥታ ሁኔታው ድንገት ሊባባስ እንደሚችል አሳስቦም ይህ ማስጠንቀቂያ አዲስ አበባን እንደማይመለከት አስታውቋል፡፡ ይሁን እንጂ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ ዜጎቹም ቢሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ገልፆ በከተማው ውስጥ የወንጀል መጠኑ ከፍተኛ መሆኑንና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች እየተካሄደ ያለው የትጥቅ ትግል ያለምንም ማስጠንቀቂያ ወደ ከተማው ሊዛመት የሚችልበት እድል እንዳለ አስታውቋል፡፡ ይህ ማስጠንቀቂያ እንዳለው የካናዳ ዜጎች ከአዲስ አበባ ውጪ ወደ አማራ፣ ትግራይና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች…
Read More
ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ ”ሳምራ” በሚል የሰየመውን የኢትዮጵያ ቡና ለገበያ አቀረበ

ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ ”ሳምራ” በሚል የሰየመውን የኢትዮጵያ ቡና ለገበያ አቀረበ

ከኢትዮጵያዊ ቤተሰቦቹ በካናዳ ተወልዶ ያደገው ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ “ዘ ዊክኤንድ”፤ የእናቱን እና የቤተሰቡን ትውልድ አገር ለማክበር በሚል በእናቱ ሥም የሰየመውን ”ሳምራ” የተሰኘ የኢትዮጵያ ቡና ለአለም ዓቀፍ ገበያ አቀረበ። አቤል ቡናውን ከ“ብሉ ቦትል ኮፊ” ጋር በመተባባር ለሽያጭ ማቅረቡን በትዊተር ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ ይፋ አድርጓል። አቤል ተስፋዬ እና የሪከርድ ኩባንያው በጋራ በመሆን “ብሉ ቦትል ኮፊ” በሚል ሥም ባቋቋሙት ድርጅት ሥር የኢትዮጵያን ባሕል እና የኢትዮጵያን ቡና በዓለም ደረጃ መሸጥ መጀመራቸውን ገልጿል፡፡ አቤል የ“ሳምራ ቡና” ወደገበያ መግባትን አስመልክቶ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ "የኢትዮጵያ ባህል የማንነቴ ወሳኙ አካል ነው” ያለ ሲሆን፤ ከ‘ብሉ ቦትል ኮፊ’ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ባሕል፣ ወጎች፣ እሴቶች እና ቡና ላይ የዓለም…
Read More