10
May
ከኢትዮጵያዊ ቤተሰቦቹ በካናዳ ተወልዶ ያደገው ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ “ዘ ዊክኤንድ”፤ የእናቱን እና የቤተሰቡን ትውልድ አገር ለማክበር በሚል በእናቱ ሥም የሰየመውን ”ሳምራ” የተሰኘ የኢትዮጵያ ቡና ለአለም ዓቀፍ ገበያ አቀረበ። አቤል ቡናውን ከ“ብሉ ቦትል ኮፊ” ጋር በመተባባር ለሽያጭ ማቅረቡን በትዊተር ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ ይፋ አድርጓል። አቤል ተስፋዬ እና የሪከርድ ኩባንያው በጋራ በመሆን “ብሉ ቦትል ኮፊ” በሚል ሥም ባቋቋሙት ድርጅት ሥር የኢትዮጵያን ባሕል እና የኢትዮጵያን ቡና በዓለም ደረጃ መሸጥ መጀመራቸውን ገልጿል፡፡ አቤል የ“ሳምራ ቡና” ወደገበያ መግባትን አስመልክቶ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ "የኢትዮጵያ ባህል የማንነቴ ወሳኙ አካል ነው” ያለ ሲሆን፤ ከ‘ብሉ ቦትል ኮፊ’ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ባሕል፣ ወጎች፣ እሴቶች እና ቡና ላይ የዓለም…