Coffee

ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ ”ሳምራ” በሚል የሰየመውን የኢትዮጵያ ቡና ለገበያ አቀረበ

ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ ”ሳምራ” በሚል የሰየመውን የኢትዮጵያ ቡና ለገበያ አቀረበ

ከኢትዮጵያዊ ቤተሰቦቹ በካናዳ ተወልዶ ያደገው ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ “ዘ ዊክኤንድ”፤ የእናቱን እና የቤተሰቡን ትውልድ አገር ለማክበር በሚል በእናቱ ሥም የሰየመውን ”ሳምራ” የተሰኘ የኢትዮጵያ ቡና ለአለም ዓቀፍ ገበያ አቀረበ። አቤል ቡናውን ከ“ብሉ ቦትል ኮፊ” ጋር በመተባባር ለሽያጭ ማቅረቡን በትዊተር ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ ይፋ አድርጓል። አቤል ተስፋዬ እና የሪከርድ ኩባንያው በጋራ በመሆን “ብሉ ቦትል ኮፊ” በሚል ሥም ባቋቋሙት ድርጅት ሥር የኢትዮጵያን ባሕል እና የኢትዮጵያን ቡና በዓለም ደረጃ መሸጥ መጀመራቸውን ገልጿል፡፡ አቤል የ“ሳምራ ቡና” ወደገበያ መግባትን አስመልክቶ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ "የኢትዮጵያ ባህል የማንነቴ ወሳኙ አካል ነው” ያለ ሲሆን፤ ከ‘ብሉ ቦትል ኮፊ’ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ባሕል፣ ወጎች፣ እሴቶች እና ቡና ላይ የዓለም…
Read More
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የቡና ሳይንስ ምሁራን ሊኖሯት ነው

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የቡና ሳይንስ ምሁራን ሊኖሯት ነው

ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ ትምህርት መስክ የተማሩ ተማሪዎች ሊመረቁ ነው። የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፤ በ2015 የትምህርት ዘመን መጨረሻ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ 37 ተማሪዎችን በ " ቡና ሳይንስ " የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን ተማሪዎች እንደሚያስመርቅ አሳውቋል። ዩኒቨርሲቲው የቡና ምርት ኢትዮጵያ ትልቁ የውጭ ምንዛሬ የምታገኝበት ሸቀጥ በመሆኑ በ2015 ዓ.ም መጨረሻ 37 ተማሪዎችን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ የትምህርት መስክ ይመረቃሉ ብሏል። ኢትዮጵያ ቡናን ለዓለም ያበረከተች ሀገር ብትሆንም እስካሁን ድረስ የቡና ትምህርት መስክ ብቁ ባለሙያዎችን ማፍራት አዳጋች ሆኖ ነበር ያለው ተቋሙ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቡና ሳይንስ ትምህርት ክፍል እራሱን ችሎ በ2012 ዓ.ም እንዲከፈት ማድረጉን አስታውሷል ። በቡና ምርት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመመርመር ከዘርፉ ተጠቃሚ…
Read More
በአዲስ አበባ የቡና አፈላል አውደ ርዕይ ሊዘጋጅ እንደሆነ ተገለጸ

በአዲስ አበባ የቡና አፈላል አውደ ርዕይ ሊዘጋጅ እንደሆነ ተገለጸ

በአዲስ አበባ የቡና አፈላል አውደ ርዕይ ሊዘጋጅ እንደሆነ ተገለጸ የኢትዮጵያዊያን ባህል ለማስተዋወቅ ዋና ዓላማው ያደረገ የኢትዮጵያ ቡቡና አፈላል ሂደትን እና ተያያዥ ባህልን የሚያሳይ አውደ ርዕይ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል። በዋርካ ኮፊ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት አማካኝነት የተዘጋጀው ይህ አውደ ርዕይ የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 9 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ይዘጋጃል ተብሏል። የድርጅቱ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሰዓዳ ሙስጠፋ በአውደ ርዕዩ ዝግጅት ዙሪያ በሰጡት መግለጫ "በዝግጅቱ ላይ የኢትዮጵያ ቡና አቆላል፣ አጠጣጥ እና ተያያዥ ባህሎች ለታዳሚያን ይቀርባል" ብልዋል። በዝግጅቱ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ መጋበዙን የሚናገሩት ወይዘሮ ሰዓዳ የኢትዮጵያን ቡና በመግዛት የሚታወቁ ሀገራት አምባሳደሮች እና ሌሎችም በእንግድነት እንደሚገኙም ጠቁመዋል። ከአዲስ አበባ ባህልና…
Read More