17
Apr
ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ ትምህርት መስክ የተማሩ ተማሪዎች ሊመረቁ ነው። የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፤ በ2015 የትምህርት ዘመን መጨረሻ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ 37 ተማሪዎችን በ " ቡና ሳይንስ " የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን ተማሪዎች እንደሚያስመርቅ አሳውቋል። ዩኒቨርሲቲው የቡና ምርት ኢትዮጵያ ትልቁ የውጭ ምንዛሬ የምታገኝበት ሸቀጥ በመሆኑ በ2015 ዓ.ም መጨረሻ 37 ተማሪዎችን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ የትምህርት መስክ ይመረቃሉ ብሏል። ኢትዮጵያ ቡናን ለዓለም ያበረከተች ሀገር ብትሆንም እስካሁን ድረስ የቡና ትምህርት መስክ ብቁ ባለሙያዎችን ማፍራት አዳጋች ሆኖ ነበር ያለው ተቋሙ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቡና ሳይንስ ትምህርት ክፍል እራሱን ችሎ በ2012 ዓ.ም እንዲከፈት ማድረጉን አስታውሷል ። በቡና ምርት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመመርመር ከዘርፉ ተጠቃሚ…