Workvisa

ኢትዮጵያዊያንን ለስራ ወደ ካናዳ መላክ የሚያስችል ስምምነት ተፈጸመ

ኢትዮጵያዊያንን ለስራ ወደ ካናዳ መላክ የሚያስችል ስምምነት ተፈጸመ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በካናዳ ከሚገኘው ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል (FFI) ጋር በክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራ መስኩ በጋራ መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱ ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች የክህሎት ልማትን ለማጠናከር፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና ዓለም አቀፍ የሥራ ዕድሎችን ለማመቻቸት ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል። በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ ከኢንቨስትመንቶች ሁሉ ትልቁ ኢንቨስትመንት የሰው ኃይል ልማት ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ነው፡፡ ስምምነቱ የሥራ ዕድል ከማመቻቸት ባሻገር ወጣቶችን በስልጠና ማብቃት ላይ ያተኮረ በመሆነ በኢትዮጵያ ወጣቶች ላይ የሚደረግ የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት ነው ብለዋል። ይህም የዜጎችን እምቅ አቅም በመፍጠር ለዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ከማቅረብ ባለፈ አጠቃላይ የሰሪ ኃይላችንን የሚያጠናክር እንደሆነም…
Read More