09
May
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የ2015 ዓ.ም. በጀት ዓመት የ9 ወር የሥራ ክንውን ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቧል፡፡ ኮሚሽኑ ባቀረበው የሥራ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባደራጃቸው ዘጠኝ የትኩረት መስኮች የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የተገኙ ውጤቶች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በዝርዝር ተካትተዋል፡፡ በቀረበው ሪፖርት የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራን በተመለከተ ኮሚሽኑ በዋናው መሥሪያ ቤቱና በከተማ ጽሕፈት ቤቶቹ በ1491 ሰዎች 1680 ጉዳዮች ላይ አቤቱታ የቀረቡለት ሲሆን ከነዚህም መካከል በኮሚሽኑ ሥልጣን ሥር የሚወድቁ 1084 አቤቱታዎችን ተቀብሎ ማስተናገዱ ተገልጿል፡፡ አቤቱታ ከቀረበባቸው ጉዳዮች መካከል አብዛኞቹ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶችን የተቀሩትደግሞ የኢኮኖሚያዊናየማኅበራዊ መብቶችንየተመለከቱ ናቸው። ኮሚሽኑ በ48 ማረሚያ ቤቶች እና በ323 ፖሊስ ጣቢያዎች አካሄድኩት ባለው…