18
Dec
ሀያላን የአውሮፓ እግር ኳስ ክለቦች የሚፋለሙበት ተወዳጁ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ቀጣይ ጨዋታዎች ድልድል ተካሂዷል፡፡ የዓምናው የቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው የእንግሊዙ ማንችስተር ሲቲ ከዴንማርኩ ኮፐንሀገን ጋር ተደልድሏል፡፡ እንዲሁም ምድቡን በበላይነት ያጠኛቀቀው አርሰናል ከፖርቹጋሉ ፖርቶ ጋር ሲደለደል ናፖሊ ከባርሴሎና፣ ፒኤስጂ ከሪያል ሶሴዳድ፣ የአምናው የፍጻሜ ተፋላሚ ኢንተር ሚላን ከአትሌቲኮ ማድሪድ፣ ፒኤስቪ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ፣ ላዚዮ ከባየር ሙኒክ እንዲሁም ላይፕዝሽ ከሪያል ማድሪድ እንደሚጫወቱ ተገልጿል፡፡ ናፖሊ ከባርሴሎና፣ ላይፕዝሽ ከሪያል ማድሪድ እና ኢንተር ሚላን ከአትሌቲኮ ማድሪድ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ከባድ ፉክክር ሊደረግባቸው የሚችሉ ጨዋታዎች እንደሚሆኑ ተጠብቋል፡፡ አራት የስፔን ክለቦች ወደ 16 ውስጥ በመግባት የቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ያለፉ ሲሆን ጣልያን ሶስት እንግሊዝ እና ጀርመን ሁለት ሁለት ክለቦቻቸው ይሳተፋሉ፡፡ የ2022/23…