11
Jun
ማንችስተር ሲቲ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አነሳ የጣልያኑ ኢንተርሚላንን እና የእንግሊዙ ማንችስተር ሲቲን ያገናኘው የዘንድሮው የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ በሲቲ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ትናንት ምሽት በቱርክ ኢስታምቡል በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ሮድሪጎ በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠራት ጎል ማንችስተር ሲቲ ዋንጫውን ማሸነፍ ችሏል፡፡ ማንችስተር ሲቲ በስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፔ ጋረዲዮላ አሰልጣኝነት ታግዞ በታሪክ የመጀመሪያውን የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ማንሳት ችሏል፡፡ ማንችሰተር ሲቲ በ2022/23 የውድድር ዓመት ከቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ በተጨማሪ የእንግሊዝን ፕሪሚየር ሊግ እና ኤፍኤካፕ ዋንጫን በማንሳት የሶትዮሽ ዋንጫ መውሰድ ችሏል፡፡ አሰልጣኝ ፔፔ ጋርዲዮላ የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ከባርሴሎና፣ ባየርንሙኒክ እና ማንችስተር ሲቲ ጋር አሸንፏል፡፡ ከቦርሲያ ዶርትሙንድ ማንችስተር ሲቲን ከአንድ ዓመት በፊት የተቀላቀለው ኖረዌያዊው አርሊንግ ሀላንድ በ12 ጎሎች…