Istanbul

ማንችስተር ሲቲ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አነሳ

ማንችስተር ሲቲ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አነሳ

ማንችስተር ሲቲ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አነሳ የጣልያኑ ኢንተርሚላንን እና የእንግሊዙ ማንችስተር ሲቲን ያገናኘው የዘንድሮው የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ በሲቲ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ትናንት ምሽት በቱርክ ኢስታምቡል በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ሮድሪጎ በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠራት ጎል ማንችስተር ሲቲ ዋንጫውን ማሸነፍ ችሏል፡፡ ማንችስተር ሲቲ በስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፔ ጋረዲዮላ አሰልጣኝነት ታግዞ በታሪክ የመጀመሪያውን የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ማንሳት ችሏል፡፡ ማንችሰተር ሲቲ በ2022/23 የውድድር ዓመት ከቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ በተጨማሪ የእንግሊዝን ፕሪሚየር ሊግ እና ኤፍኤካፕ ዋንጫን በማንሳት የሶትዮሽ ዋንጫ መውሰድ ችሏል፡፡ አሰልጣኝ ፔፔ ጋርዲዮላ የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ከባርሴሎና፣ ባየርንሙኒክ እና ማንችስተር ሲቲ ጋር አሸንፏል፡፡ ከቦርሲያ ዶርትሙንድ ማንችስተር ሲቲን ከአንድ ዓመት በፊት የተቀላቀለው ኖረዌያዊው አርሊንግ ሀላንድ በ12 ጎሎች…
Read More
ማንችስተር ሲቲ እና ኢንተርሚላን ለአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ አለፉ

ማንችስተር ሲቲ እና ኢንተርሚላን ለአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ አለፉ

በአውሮፓ ምርጥ እግር ኳስ ክለቦች ሙካከል ሲካሄድ የቆየው የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ተፋላሚዎች ታውቀዋል። ትናንት ምሽት በእንግሊዝ ማንችስተር ከተማ በሪያል ማድሪድ እና ማንችስተር ሲቲ መካከል የተካሄደው ውድድር በሲቲ የበላይነት ተጠናቋል። በርናርዶ ሲልቫ ሁለት ጎል፣ አልቫሬዝ እና ሚሊታኦ በራሱ ግብ ላይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ሲቲ በቱርክ ኢስታምቡል ከተማ ለሚካሄደው የፍጻሜ ውድድር ማለፍ ችሏል። የጣልያኑ ኢንተር ሚላን በፍጻሜው ማንችስተር ሲቲን የሚገጥም ሲሆን ጨዋታው ሰኔ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት 4:00 ላይ ይካሄዳል ተብሏል። የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድርን የስፔኑ ሪያል ማድሪድ 14 ጊዜ በማሸነፍ ቀድሚው ክለብ ሆኖ ተመዝግቧል። የፍጻሜ ተፋላሚው ማንችስተር ሲቲ እስካሁን አንድም ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግን ያላሸነፈ ሲሆን ሌላኛው የፍጻሜ ተፋላሚ ኢንተርሚላን ሶስት…
Read More