OAU

ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲዋን ከማለዘብ ወደ ማሳመን መቀየሩን ገለጸች

ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲዋን ከማለዘብ ወደ ማሳመን መቀየሩን ገለጸች

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ በሰሜኑ ጦርነት ውስጥ በነበረችበት ወቅት  የደረሱ ዓለም አቀፍ ጫናዎችን ለመቋቋም "የማለዘብ ዲፕሎማሲ" ስትከተል መቆየቷን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ እና ተጨማሪ የዲፕሎማሲ ስራዎች በመሰራታቸው ይደርሱ የነበሩ ጫናዎች መቀነሳቸውን ቃል አቀባዩ ጠቅሰዋል። ይህን ተከትሎም ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከማለዘብ ዲፕሎማሲ ወደ ማሳመን ዲፕሎማሲ መመለሷን የተናገሩት አምባሳደር መለስ የተለያዩ የዓለማችን ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማሻሻል መሪዎቻቸውን ወደ አዲስ አበባ በመላክ ላይ መሆናቸውን አክለዋል። የአፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ ከተማም ከኒዮርክ እና ጀኔቫ በመቀጠል ሶስተኛዋ የዓለማችን የዲፕሎማሲ ከተማ ይዞታዋ መመለሷን ቃል…
Read More