17
May
ደርጅቱ በቀጣዮቹ አምስት አመታት ውስጥ 10 ሺህ ቤቶችን እንደሚገነባ አስታውቋል፡፡ ከ30 አመታት በላይ በመኖሪያ ቤት ግንባታ እና በኮንስትራክሽን ዘርፉ የተሰማራዉ ፍሊንትስቶን ሪልስቴት 10 ሚሊዮን አክሲዮኖችን ለገበያ ማቅረቡን አስታዉቋል። የፍሊንትስቶን መስራችና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ጸደቀ ይሁኔ እንደተናገሩት ከ20 ሺህ ብር ጀምሮ እስከ 2 ሚሊዮን ብር ድረስ ዋጋ ያላቸዉን አክሲዮኖች ለሽያጭ መቅረባቸዉን ተናግረዋል። የአንዱ አክሲዮን ዋጋም 1 ሺህ ብር መሆኑን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል። ከሚቀጥለው ሐምሌ ጀምሮ ሽያጩ ይጀመራል የተባለ ሲሆን ባለ አክሲዮኖች ባላቸዉ የድርሻ መጠን ተሰልቶ አልያም በፍላጎታቸዉ ተጨማሪ ገንዘብ ከፍለዉ የቤት ባለቤት መሆን የሚችሉበት እድል መመቻቸቱን ገልጸዋል፡፡ በዋነኛነት አክሲዮን ሽያጩ ያስፈለገዉ ተጨማሪ ካፒታል ለማግኘት ፣ ድርጅቱን ከ አምስት ሰዎች የሽርክና ባለቤትነት…