mosquedemolitions

በሸገር ከተማ አስተዳድር ከ10 በላይ መስጅዶች መፍረሳቸው ተገለጸ

በሸገር ከተማ አስተዳድር ከ10 በላይ መስጅዶች መፍረሳቸው ተገለጸ

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በጉዳዩ ዙሪያ ጣልቃ እንዲገቡ  ተጠይቀዋል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በቅርቡ በአዲስ አበባ ዙሪያ "ሸገር ከተማ" ተብሎ በተመሠረተው ከተማ መስጅዶች እየፈረሱ መሆናቸውን ገልጿል። የመስጂድ ፈረሳው መቀጠሉን ተከትሎም  "አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠው" የሚጠይቅ ደብዳቤ ምክር ቤዩ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጽፏል። ምክር ቤቱ በደብዳቤው፤ በከተማ አስተዳደሩ "ህገወጥ" በሚል በርካታ መስጂዶች እየፈረሱበት እንደሚገኙና፣ በጉዳዩ ላይ ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጋር በስልክ በመነጋገር መፍትሄ ላይ ደርሶ እንደነበር ገልጿል። ነገር ግን "የከተማ አስተዳደሩ በረመዳን ወር ለጊዜው የመስጂድ ፈረሳውን እንዲቆም በማድረግ ከረመዳን በኋላ የመስጅዶች ፈረሳ በአዲስ መልከ በብዛት ቀጥሏል"  ብሏል። ምክር ቤቱ በመግለጫው የመስጅድ ፈረሳ ጉዳይ በከተማ አስተዳደሩ "ህገ ወጥ" ስለተባለ…
Read More