19
Sep
190 እስረኞች ታመው ህክምና ሲወስዱ ሶስት ሰዎች ደግሞ በጽኑ ህክምና ክትትል ውስጥ መሆነቸውን ኢሰመኮ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ወይም ኢሰመኮ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳድር ስር ባለ ሲዳሞ አዋሽ የታሰሩ ሰዎችን አስመልክቶ ያደረገውን ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ኮሚሽኑ ነሐሴ 24 እንዲሁም በጳጉሜን 2 እና 3 ቀን 2015 ዓ.ም. በዚህ ማቆያ ማእከል/ቦታ ባደረገው ጉብኝት እንዲሁም፣ በማቆያ ማእከሉ የሚገኙ ሰዎችን እና የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮን ጨምሮ የሚመለከታቸውን የመንግሥት የጸጥታ አካላት በማነጋገር ክትትል አካሂጃለሁ ብሏል። በተጨማሪም የማቆያ ማእከሉ አስተባባሪዎች እና ጥበቃ ሲያደርጉ የነበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላትን፣ በቦታው የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ የሕክምና ባለሞያዎችን እና ተጨማሪ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኝ የነበረውን የጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ኃላፊዎችን እና ባለሞያዎችን በማነጋገር…