11
Jul
በሸገር ከተማ አስተዳደር በሚገኘው ኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ለባለእድለኞች በተላለፉ ቤቶች ውስጥ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች ቁልፍ ሰብረው በመግባት ወረራ እየፈጸሙ መሆኑን የኮንዶሚኒየሙ ሕጋዊ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ በኮንዶሚኒየሙ የእጣ እድለኞች ሆነው ለባለቤቶች ቁልፍ ተላለፈው፤ ነገር ግን ተቆልፈው በተቀመጡ ቤቶች እና እስካሁን ለባለእድለኞች ባልተላለፉ ቤቶች ላይ የማይታወቁ ሰዎች ወረራ እየፈጸሙ ነው ተብሏል። ይህን ድርጊት ለመከላከል ጥረት በሚያደርጉ የኮንዶሚኒየም የጥበቃ ሠራተኞች ላይም ዛቻ እና ማስፈራሪያ በማድረስ ሰዎቹ በኃይል እየገቡ መሆናቸውን አዲስ ማለዳ ዘግቧል፡፡ ነዋሪዎቹ አክለውም፤ “ተዘግቶ የተቀመጠን ቤት በኃይል ሰብረው ገብተው ወረራ ሲፈጽሙ አንድም የመንግሥት አካል ሊያሰቆማቸው የሞከረ የለም፡፡” ሲሉ ተደምጠዋል። ከመጋቢት 2015 ጀመሮ በኮንዶሚኒየሞቹ ላይ ከፍተኛ ወረራ እየተካሄደ መሆኑን በመጠቆምም፤ “ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል በተደጋጋሚ…