02
Jun
በአዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ ባለው አንዋር መስጅድ ዛሬ ምሳ ሰዓት አካባቢ የጸጥታ ችግር መከሰቱ ይታወቃል። ለአርብ ወይም ጁመዓ ጸሎት በስፍራው የነበሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዳሉን ከሆነ የሶላት ስነ ስርዓቱ ተጠናቆ ወደ ውጪ እየወጡ እያለ ከጸጥታ ሀይሎች ጥይት መተኮሱን ተከይሎ በአካባቢው ችግር ተፈጥሯል። ለደህንነቱ በመፍራት ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የአይን እማኝ ለአልዐይን እንዳለው " በአንዋር መስጅድ የጁመዓ ስግደትን ስግደት ጨርሰን ወደ ውጪ እየወጣን እያለ ፖሊሶች ጥይት ተኮሱ፣ ከዚያም ሰዎች መውደቅ እና መጮህ ጀመሩ" ሲል ነግሮናል። "አጠገቤ የነበሩ ሁለት ሰዎች እጅ እና እግራቸውን በጥይት ተመተው ሲወድቁ አይቻለሁ" ያለን ይህ የአይን እማኝ እኔ ወደ መስጅዱ ተመልሼ በመግባቴ ተርፌያለሁ ሲልም የአይን እማኙ አክሏል። "ምንም አይነት…