Islam

ኢትዮጵያ የእስላማዊ አገራት ትብብር ድርጅትን ልትቀላቀል ነው ተባለ

ኢትዮጵያ የእስላማዊ አገራት ትብብር ድርጅትን ልትቀላቀል ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ዋና መቀመጫውን ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ካደረገው ዓለም አቀፉ የእስላማዊ ሀገራት ትብብር ድርጅት አባል ለመሆን እንቅስቃሴ መጀመሯ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ ከድርጅቱ አባል ሀገራት መካከል የተወሰኑትን ድጋፍ አግኝታለችም ተብሏል፡፡ የኦርጋናይዜሽን ኦፍ እስላሚክ ኮፕሬሽን  ወይም የእስላማዊ አገራት ትብብር ድርጅት 57 ሀገራትን በአባልነት የያዘ ስብስብ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የዚህ ድርጅት አባል ለመኾን ከድርጅቱ ጋር ንግግር መጀመሯን ዋዜማ ዘግቧል። በቻዳዊው ሂሴን ብራሂም ታሃ የሚመራው ድርጅቱ በዓለም ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቀጥሎ በአባላት ብዛት ትልቁ የበይነ መንግሥታት ማኅበር ነው። ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ለመኾን ንግግር የጀመረችው፣ ከድርጅቱ በቀረበላት ግብዣ መሠረት እንደኾነም ተገልጿል። ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ለመኾን በጀመረችው እንቅስቃሴ የቱርክን፣ ፓኪስታንን እና የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶችን ድጋፍ አግኝታለች ተብሏል። ከአፍሪካ ጅቡቲ፣…
Read More
ቱርክ በጦር መሳሪያ የተጎዳው አል ነጃሺ መስጅድን ለማደስ ጥያቄ አቀረበች 

ቱርክ በጦር መሳሪያ የተጎዳው አል ነጃሺ መስጅድን ለማደስ ጥያቄ አቀረበች 

 ታሪካዊው የኢትዮጵያ ቅርስ አል ነጃሺ መስጅድ በትግራይ ክልል የሚገኝ ሲሆን በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት ወቅት በከባድ መሳሪያ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ቱርክ ይህንን ታሪካዊ የእስልመና ቅርስ ለማደስ ለኢትዮጶያ መንግስት ጥያቄ እንዳቀረበች የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን  አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ እና የትግራይ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ቅርሱ በሚታደስበት ሁኔታ ከቱርክ የቀረበውን ጥያቄ መቀበላቸው ተገልጿል፡፡ ቅርሱ በሚታደስበት ሁኔታም የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጀምረዋል የተባለ ሲሆን የቱርክ ቅርስ ጥገና ባለሙያዎች ወደ ቦታው አምርተው ምልከታ መጀመራቸውን የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አበባው አያሌው ተናግረዋል፡፡  ለቅርሱ እድሳት የሚያስፈልገው በጀት ምን ያህል እንደሆነ እና ምን ያህል ገንዘብ እንደሚፈጅ ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡ ለሁለት ዓመት በተካሄደው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት አል ነጃሺ መስጂድ…
Read More
በአዲስ አበባ አንዋር መስጅድ የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

በአዲስ አበባ አንዋር መስጅድ የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

በአዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ ባለው አንዋር መስጅድ ዛሬ ምሳ ሰዓት አካባቢ የጸጥታ ችግር መከሰቱ ይታወቃል። ለአርብ ወይም ጁመዓ ጸሎት በስፍራው የነበሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዳሉን ከሆነ የሶላት ስነ ስርዓቱ ተጠናቆ ወደ ውጪ እየወጡ እያለ ከጸጥታ ሀይሎች ጥይት መተኮሱን ተከይሎ በአካባቢው ችግር ተፈጥሯል። ለደህንነቱ በመፍራት ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የአይን እማኝ ለአልዐይን እንዳለው " በአንዋር መስጅድ የጁመዓ ስግደትን ስግደት ጨርሰን ወደ ውጪ እየወጣን እያለ ፖሊሶች ጥይት ተኮሱ፣ ከዚያም ሰዎች መውደቅ እና መጮህ ጀመሩ" ሲል ነግሮናል። "አጠገቤ የነበሩ ሁለት ሰዎች እጅ እና እግራቸውን በጥይት ተመተው ሲወድቁ አይቻለሁ" ያለን ይህ የአይን እማኝ እኔ ወደ መስጅዱ ተመልሼ በመግባቴ ተርፌያለሁ ሲልም የአይን እማኙ አክሏል። "ምንም አይነት…
Read More
በአዲስ አበባ ለሰላማዊ ሰልፍ ወደ አደባባይ የወጡ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

በአዲስ አበባ ለሰላማዊ ሰልፍ ወደ አደባባይ የወጡ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

ፖሊስ በስፍራው በተፈጠረ ረብሻና ግርግር የሰው ሕይወት ማለፉን ገልጿል። በአዲስ አበባ ከተማ አንዋር መስጂድ የጁምዓ ሶላት ከተጠናቀቀ በኋላ በሌሎች አካባቢዎች መስጂዶች ፈርሰዋል በሚል ምክንያት በመርካቶ ዙሪያ በተፈጠረ ረብሻና ግርግር የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። ፖሊስ ባወጣው መግለጫ በተፈጠረው ረብሻና ግርግር ህግ በማስከበር መደበኛ ሥራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱንም አስታውቋል። በተለይም በተለምዶ ጋዝ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተፈጥሮ በነበረ ግርግር ሁለት ግለሰቦች ጉዳት ደርሶባቸው ለህክምና ሆስፒታል ከተላኩ በኋላ ሕይወታቸው አልፏል ተብሏል። በተጨማሪም አራት ግለሰቦች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ህግን ለማስከበር በተሰማሩ 37 የፖሊስ አመራርና አባላት እንዲሁም 15 የሚሆኑ የተለያዩ የፖሊስ አጋዥ ሀይሎች ከባድና ቀላል…
Read More