OIC

ኢትዮጵያ የእስላማዊ አገራት ትብብር ድርጅትን ልትቀላቀል ነው ተባለ

ኢትዮጵያ የእስላማዊ አገራት ትብብር ድርጅትን ልትቀላቀል ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ዋና መቀመጫውን ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ካደረገው ዓለም አቀፉ የእስላማዊ ሀገራት ትብብር ድርጅት አባል ለመሆን እንቅስቃሴ መጀመሯ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ ከድርጅቱ አባል ሀገራት መካከል የተወሰኑትን ድጋፍ አግኝታለችም ተብሏል፡፡ የኦርጋናይዜሽን ኦፍ እስላሚክ ኮፕሬሽን  ወይም የእስላማዊ አገራት ትብብር ድርጅት 57 ሀገራትን በአባልነት የያዘ ስብስብ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የዚህ ድርጅት አባል ለመኾን ከድርጅቱ ጋር ንግግር መጀመሯን ዋዜማ ዘግቧል። በቻዳዊው ሂሴን ብራሂም ታሃ የሚመራው ድርጅቱ በዓለም ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቀጥሎ በአባላት ብዛት ትልቁ የበይነ መንግሥታት ማኅበር ነው። ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ለመኾን ንግግር የጀመረችው፣ ከድርጅቱ በቀረበላት ግብዣ መሠረት እንደኾነም ተገልጿል። ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ለመኾን በጀመረችው እንቅስቃሴ የቱርክን፣ ፓኪስታንን እና የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶችን ድጋፍ አግኝታለች ተብሏል። ከአፍሪካ ጅቡቲ፣…
Read More