Greenethiopia

የአዳማ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች የአንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት አሸነፉ

የአዳማ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች የአንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት አሸነፉ

አቢሲኒያ ባንክ ለሶስት እንስቶች አንድ ሚሊዮን ብር ሸለመ ባንኩ "አሚን አዋርድ" በሚል የሰየመውን የሥራ ፈጠራ ውድድር አጠናቋል፡፡ ውድድሩ ካሳለፍነው ህዳር ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ በሥራ ፈጠራቸው ይዘት እና ችግር ፈቺነታቸው ለተመረጡ 5 ተወዳዳሪዎች የእውቅናና የሽልማት መርሐ-ግብር በአዳማ ከተማ ተካሂዷል፡፡ በውድድሩ ላይ ከ1ኛ - 5ኛ ለወጡ ተሳታፊዎች በአጠቃላይ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የተሸለሙ ሲሆን ከ6ተኛ እስከ 20ኛ ድረስ ለወጡ ተሳታፊዎችም የማበረታቻ ሽልማት መሰጠቱን አቢሲኒያ ባንክ ለኢትዮ ነጋሪ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ የአንደኝነት ደረጃን በማግኘት የ1,000,000 ብር ተሸላሚ የሆኑት በአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የነበሩ ሦስት እንስቶች አሸንፈዋል፡፡ እንስቶቹ ‹ግሪን ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ማዳበሪያ› በሚል በጋራ ባቋቋሙት ድርጅት ስም አሸናፊ በመሆን ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል፡፡
Read More