18
May
በሳሙኤል አባተ የኮሌራ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ አራት ክልሎች መዛመቱን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል። በደቡብ ክልል ልዩ ልዩ ዞኖች እና ወረዳዎች ደግሞ በወረርሽኙ ከተጠቁ 920 ሰዎች መካከል የ18 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል። የጤና ጥበቃ ሚንስቴርም ወረርሽኙ በተስፋፋባቸው አካባቢዎች ክትባት መስጠት ተጀምሯል። በኢትዮጵያ፣ የኮሌራ ወረርሽኝ፣ በአራት ክልሎች መዛመቱን ያስታወቀው የጤና ሚኒስቴር፣ ወረርሽኙን ለመከላከል፣ ለ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች ክትባት እንደሚሰጥ አመልክቷል፡፡ በኢትዮጵያ አራት ክልሎች ተዛምቶ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘው ይህ ወረርሽኝ በዐዲስ መልክ በተከሠተባቸው የደቡብ ክልል አምስት ዞኖች እና ሦስት ልዩ ወረዳዎች ተስፋፍቷል ተብሏል። የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ወረርሽኙ፥ በአገር አቀፍ ደረጃ በአራት ክልሎች መከሠቱን አረጋግጠዋል። ወረርሽኙ ከተስፋፋባቸው ክልሎች መካከልም ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ሶማሊ…