Nationalfootball

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ዋልያዎቹን በአሰልጣኝነት ተረከቡ

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ዋልያዎቹን በአሰልጣኝነት ተረከቡ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሐየራዊ ቡድን አሰልጣን የነበሩት ገብረመድህን ሀይሌ በድጋሚ ዋልያዎቹን እንዲያሰለጥኑ ተመርጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው የኢትዮጵያ መድን እግር ኳ ክለብን በማሰልጠን ላይ የነበሩት አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ በአንድ ዓመት ውል ብሔራዊ ቡድኑን እንዲያሰለጥኑ ተመርጠዋል፡፡ አሰልጣኙ የብሔራዊ ቡድን ስራቸውን ከኢትዮጵያ መድን እግር ኳስ ክለብ ጋር ደርበው እንዲያካሂዱ ከፌዴሬሽኑ ጋር እንደተስማሙም ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ የሚያደርጋቸውን ሁለት ቀጣይ የሜዳው ጨዋታዎችን ወደ ሞሮኮ ተጉዘው ያካሂዳሉም ተብሏል። የመጀመርያው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ከሴራሊዮን ኅዳር 5 እንዲሁም ሁለተኛው ጨዋታ ከቡርኪና ፋሶ ጋር ኅዳር 11 የሚደረግ ሲሆን ሁለቱም ጨዋታዎች በሞሮኮ ኤል አብዲ ስታዲየም ይደረጋሉ፡፡ ብሄራዊ ቡድኑን በኢንተርናሽናል ውድድር ተፎካካሪ ማድረግ የሚጠብቅባቸው አሰልጣኝ ገብረመድህን…
Read More
ሳላሀዲን ሰኢድ ጫማውን ሰቀለ

ሳላሀዲን ሰኢድ ጫማውን ሰቀለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ ግብ አግቢ ሳላሀዲን ሰዒድ ኳስ መጫወት ማቆሙን ገልጿል በአሶሳ ተወልዶ ያደገው ሳላሀዲን ለበርካታ የውጪ እና የሀገር ውስጥ ክለቦች መጫወት ችሏል ሳላሀዲን ሰኢድ ጫማውን ሰቀለ። በተለያዩ ክለቦች እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለበርካታ አመታት በመጫወት የሚታወቀው ገልግሎት ሳላዲን ሰዒድ ጫማውን ሰቅሏል፡፡ ላለፉት 15 ዓመታት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ አይረሴ ታሪኮችን ያስመዘገበው ሳላዲን እግር ኳስ መጫወቱን እንዳቆመ ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል። ተጫዋቹ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባለፈ ለሙገር ሲሚንቶ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ለሲዳማ ቡና እንዲሁም ከውጪ ደግሞ ለግብጾቹ ዋዲዳግላ እና አልአህሊ፣ ለአልጀሪያው መውሊዲያ አሊደር እና ለቤልጂየሙ ሊርስ እግር ኳስ ክለቦች መጫወት ችሏል። በ37 ዓመቱ ራሱን ከእግር ኳስ ጨዋታ ያገለለው ሳላዲን በተያዘው ዓመት…
Read More
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጊዜያዊ አሰልጣኝ ተሾመ

ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጊዜያዊ አሰልጣኝ ተሾመ

ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸው ተገልጿል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ቡድኑን በጊዜያዊነት የሚመሩ አሰልጣኞችን ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ቡድኑን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲመሩ ከቆዩት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ ቀጣዩን አሰልጣኝ ለመምረጥ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውይይት ማድረጉን ገልጿል። በዚሁ መሰረት ኮሚቴው በቴክኒክ ዳይሬክተርነት እየሰሩ የሚገኙትን ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት ቀጣይ ጨዋታዎችን እንዲመሩ ከውሳኔ ላይ መድረሱን አመልክቷል። በተጨማሪ ኮሚቴው ኢንስትራክተር ዳንኤልን እንዲያግዙ በፕሪምየር ሊጉ በመስራት ላይ የሚገኙትና በወቅታዊ ውጤታማነት የተሻሉ ሆነው ተገኝተዋል ያላቸውን የባህር ዳር ከተማ አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ምክትል አሰልጣኝ ሆነው እንዲሰሩ መወሰኑን ጠቅሷል። ፌዴሬሽኑ…
Read More