ዜና

በአማራ ክልል በሶስት ወራት ውስጥ 120 ንጹሀን ዜጎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ፡፡

በአማራ ክልል በሶስት ወራት ውስጥ 120 ንጹሀን ዜጎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ ክልሎች ያደረጋቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ኮሚሽኑ እንደለጸው ሪፖርቱ ከመስከረም ወር አጋማሽ 2017 ዓ.ም እስከ ታኅሣሥ 2017 ዓ.ም አጋማሽ ባለው ጊዜ ውስጥ ያለውን ጊዜ የሚመለከት ነው ብሏል፡፡ ሪፖርቱ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በግጭት ዐውድ ውስጥ ባሉ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን  በሙሉ የሚሸፍን አይደለም ያለው ኮሚሽኑ በእነዚህ አካባቢዎች በነጻነት ተንቀሳቅሶ የተሟላ ክትትልና ምርመራ ለማካሄድ ምቹ ሁኔታ ባለመኖሩ፣ ውጤታማ ክትትልና ምርመራ የተከናወነባቸውን ጉዳዮች ብቻ በማሳያነት እንዳቀረበም ገልጿል፡፡ ኢሰመኮ በሪፖርቱ ላይ እንደጠቀሰው በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች ከደረሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች አሳሳቢ ሆነው ከቀጠሉ ጉዳዮች መካከልም ከፍርድ ውጭ ግድያ መፈጸም፣ በግጭት ዐውድና አካባቢ የሚደርስ የሲቪል…
Read More
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቁርዓን ውድድር ልታስተናግድ ነው

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቁርዓን ውድድር ልታስተናግድ ነው

በኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ የቁርአን እና አዛን ውድድር ጥር 25 እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቁርኣንና የአዛን ውድድር ሽልማት 2ኛ ዙር 2025 ውድድርን ምክንያት በማድረግ በርካታ ሀገራት እንግዶችና ቱሪስቶች በውድድሩ ላይ ለመታደም እንደሚመጡ የዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ኑረዲን ቃሲም ተናግረዋል። የፊታችን ሰኞ ጥር 19 ቀን 2017 ከ 60 ሀገራት 100 ተወዳዳሪዎች እንዲሁም 11 ዳኞች ከሁሉም አህጉር ኢትዮጵያ የሚገቡ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክብር እንግዶች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ ዳግም እንደሚገኙ ተገለጿል፡፡ ይህ መድረክ ቱሪስቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለመሣብ ቀላል የማይባል ሚና ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የቱሪዝም ሚኒስትር፣ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን…
Read More
ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ባትሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ልታቋቁም መሆኗ ተገለጸ

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ባትሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ልታቋቁም መሆኗ ተገለጸ

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸሙን ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ለሚኒስትሩ ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል በኢትዮጵያ  የኤልክትሪክ መኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች ቁጥራቸው እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ የመለዋወጫ አካላት ፍላጎትን እንዴት ሊሸፈን ታስቧል? የሚለው ዋነኛው ነበር፡፡ ከኤሌክትሪክ መኪና ውስጥ የባትሪ ጉዳይ ዋናው በመሆኑ ወደ ፊት ለባትሪ የሚወጣው ውጪ ምንዛሪ ፈታኝ እንዳይሆን በሃገር ውስጥ ለማምረት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ምን እየሰራ ነው ሲሉም የምክር ቤቱ አባላት ጠይቀዋል፡፡ አቶ መላኩ በምላሻቸው የኤሌክትሪክ መኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች በክልሎችም ጭምር እየጨመረ መምጣቱን መልካም ነው ምክንያቱም ሃገሪቱ በየአመቱ ለነዳጅ የምታወጣውን 4 ቢልዮን ዶላር ያስቀራል ብለዋል፡፡ የኤሌክትሪክ መኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች እየበረከቱ…
Read More
ጎንደር ዩንቨርስቲ የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመት እያከበረ ነው

ጎንደር ዩንቨርስቲ የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመት እያከበረ ነው

ጎንደር ዩንቨርስቲ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ 100 ሺህ ተማሪዎችን እንዳስመረቀ ተገልጿል። ዩንቨርሲቲው በኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ዕጥረት ለመፍታት በሚል በ1947 ዓ.ም መመስረቱም ተገልጿል። የዩንቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አጸደወይን እንዳሉት ዩንቨርሲቲው በ70 ዓመት ታሪኩ 100 ሺህ ተማሪዎችን አሰልጥኖ አስመርቋል ብለዋል። በኢትዮጵያ የሐኪሞች ዕጥረትን ተከትሎ የውጭ ሀገራት የህክምና ባለሙያዎች ወደ ሀገር ውስጥ ይገቡ ይነበረ ሲሆን ጎንደር ዩንቨርሲቲ ይህ ችግር በቋሚነት እንዲፈታ የራሱን አስተዋጽኦ መወጣቱም ተጠቅሷል። ጎንደር ዩኒቨርስቲ ሕንፃ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገነባ መሬታቸውን ለሰጡ ግለሰቦች ዕውቅና በመስጠት የአርሶ አደሮች ቀንን እሰይማለሁም ብሏል። በተመሳሳይ በተለያየ መንገድ አሰተዋፅኦ ላደረጉለት ግለሰቦች የሕንፃ፣ የመንገድና የአዳራሽ ስያሜ ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል። ፕሬዚዳንቱ በመግለጫቸው ስያሜው በዩኒቨርስቲውና በሆስፒታሉ ታሪክ ጉልህ ድርሻ ለነበራቸው ግለሰቦች፣…
Read More
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ  ሠራተኞች  የሥራ ማቆም አድማ ላይ መቱ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ  ሠራተኞች  የሥራ ማቆም አድማ ላይ መቱ

400 ያህል የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ የጥሪ ማዕከል ሠራተኞች "አይሶን ኤክስፔሪያንስ" የተሰኘ ወኪል ድርጅት ይፈጸምብናል ባሉት የአስተዳደር በደል ሳቢያ ላለፉት 2 ቀናት የሥራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸውን ዋዜማ ዘግቧል። ሠራተኞቹ በዋናነት የሥራ ማቆም አድማ ያደረጉት፤ በወኪል ድርጅቱ በኩል የሚከፈላቸው ደመወዝ ዝቅተኛ በመሆኑ እንደሆነ ታውቋል። ወኪል ድርጅቱ ከፍተኛ ደመወዝ ተከፋይ ሠራተኞችን በተጠና መልኩ ከሥራ እንዲሰናበቱ እያደረገ እንደሆነና ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ብቻ 80 ያህል ሠራተኞችን ሕጋዊነቱን ባልተከተለ መንገድ እንዳሰናበተ ተነግሯል ። ተመሳሳይ የሥራ ዓይነት ለሚሠሩ ሠራተኞች፣ ቋንቋንና ማንነትን መሠረት ያደረገ ሕገወጥ የደመወዝ ልዩነትና አድሎ እንዳለና ድርጅቱ ችግሩን እንዲያስተካክል በተደጋጋሚ ተጠይቆ ሊያስተካክል እንዳልቻለ የድርጅቱ ሰራተኛ ማኅበር አስታውቋል ። የድርጅቱ እህት ኩባንያ የሆነው ሳፋሪኮም…
Read More
ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ከሚያስሩ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ተካተተች

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ከሚያስሩ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ተካተተች

በመላው አፍሪካ 67 ጋዜጠኞች በስራቸው ምክንያት ብቻ መታሰራቸውን አለም አቀፉ የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ (ሲፒጄ) ሪፖርት ያስረዳል። የተመዘገበው እስር በአፍሪካ በነጻ ሀሳብን የመግለጽ መብት ፣ የመረጃ ነጻነት እና ሌሎችም መብቶች እያሽቆለቆሉ እንደሚገኙ ማሳያ ነው ብሏል ሪፖርቱ ፡፡ ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ሲፒጄ እስከ ታህሳስ 1 ቀን ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ 361 ጋዜጠኞች መታሰራቸውን የገለጸ ሲሆን በአፍሪካ የተመዘገበው ዕስር እስከዛሬ ከነበሩት በመጠኑ ሁለተኛው ነው ተብሏል። በሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ሙቶኪ ሙሞ “መንግስታት በጋዜጠኞች ላይ የብሔራዊ ደህንነት፣ የፀረ-ሽብርተኝነት እና የሳይበር ወንጀል ህጎችን በመሳሪያነት በመጠቀም ጋዜጠኞችን ለማሳደድ እና ለማሰር እያዋሉት እንደሚገኙ” ተናግረዋል፡፡ አስተባባሪው እነዚህ አዝማሚያዎች በአፍሪካ ብቻ የተገደቡ ባይሆኑም በአህጉሪቱ በእንደዚህ አይነት ህጎች ክስ የሚመሰረትባቸው…
Read More
ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ የሌላቸው ድርጅቶች መኪና ወደ ሀገር ውስጥ እንዳያስገቡ ከለከለች

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ የሌላቸው ድርጅቶች መኪና ወደ ሀገር ውስጥ እንዳያስገቡ ከለከለች

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሙያ ጣቢያ ለመቀየር ጥናት እየተደረገ  መሆኑን የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወርቁ ደስታ እንዳሉት  "በሁለተኛው ምዕራፍ እየተከናወነ ባለው የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት በመኪና ማቆሚያዎች የኃይል መሙያ እየተሠራ ነው " ብለዋል።የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ዴዔታ በርኦ ሀሰን በበኩላቸው "ከዚህ በኃላ የተሽከርካሪ አስመጪና የሚገጣጥሙ ድርጅቶች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል መሙያ ሳይተክሉ በሥራ ላይ መሰማራት አይችሉም " ብለዋል።በኢትዮጵያ ከ400 በላይ ተቋማት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ እያስመጡና እየገጣጠሙ ነው የተባለ ሲሆን ሁሉም አስመጪዎች እና ገጣጣሚዎች የኃይል መሙያ እንዳላቸውም ተገልጿል። ኢትዮጵያ ከአንድ ሳምንት በፊት  ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሃይል መሙያ ማሽን (ቻርጀር) መትከል የሚፈቅድ መመሪያ ማዘጋጀቷ…
Read More
ኢትዮጵያ ከ14 ሺህ በላይ ለውጭ ሀገራት ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ ሰጠች

ኢትዮጵያ ከ14 ሺህ በላይ ለውጭ ሀገራት ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ ሰጠች

ሀገሪቱ ለ20 የውጭ ዜግነት ለነበራቸው ሰዎች የኢትዮጵየዊ ዜግነት ሰጥታለች ተብሏል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የተቋሙን የስድስት ወራት አፈጻጸም አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ዳይሬክተሯ በመግለጫቸው ላይ እንዳሉት ለ14 ሺህ 367 ለሚሆኑ የውጭ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለ20 ግለሰቦች ደግሞ የኢትዮጵያዊ ዜግነት እንደተሰጣቸውም ወይዘሮ ሰላማዊት በመግለጫው ለይ ጠቅሰዋል። ተቋሙ ለዜጎች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት የሠው ሀይሉን የማጠናከር፤ አሰራሩን በቴክኖሎጂ የማገዝ ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ለጉብኝት ቱሪስት፣ ለኮንፍረንስና ለቢዝነስ የሚገቡትን ለማስተናገድ በ188 ሀገራት ቪዛ ኦን አራይቫል በመክፈት እየተሰራ መሆኑም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሚሊዮን በላይ ሰዎች በአየር ትራንስፖርት ወደ ኢትዮጵያ…
Read More
የህዳሴው ግድብን ለማጠናቀቅ 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተባለ

የህዳሴው ግድብን ለማጠናቀቅ 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተባለ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ቀሪ ስራዎች ለማጠናቀቅ 80 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው ተገልጿል፡፡ ከ14 ዓመት በፊት ለግንባታው መሰረት ድንጋይ ሲጣል 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል ተብሎ የተጀመረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ፤ ግንባታው 97.6 በመቶ እንደደረሰና ጥቂት የማጠናቀቂያ ስራዎች ብቻ እንደቀሩት  የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ የፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ተናግሯል፡፡ ህዝቡ እስካሁን ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ለግእቡ ግንባታ በበጎ ፈቃደኝነት ያዋጣ ሲሆን በዚህ ዓመት 1.6 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የዚህ አካል የሆነና ባንኮችን፣ ኢንሹራንስ ተቋማትንና የብድርና ቁጠባ ተቋማትን ያሳተፈ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ባሳለፍነው ዓርብ አካሂዷል፡፡ በመርሃ ግብሩ 110 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ የታሰበ ቢሆንም በወቅቱ ከተቋማቱ መሰብሰብ የተቻለው 25.9 ሚሊዮን ብር ብቻ…
Read More
አሲያ ኽሊፋ የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር አለም አቀፍ አምባሳደር ሆና ተመረጠች

አሲያ ኽሊፋ የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር አለም አቀፍ አምባሳደር ሆና ተመረጠች

ኢትዮጵያዊቷ ተማሪ የ2025 ሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር አለም አቀፍ አምባሳደር ሆና ተመርጣለች፡፡ የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ዓመታዊ የስልጠና መርሃ ግብር፣ ከሁዋዌ ታዋቂ የማኅበራዊ ኃላፊነት ስራዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ይህ ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት የ2025 የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር አለም አቀፍ አምባሳደሮችን መርጦ አሳውቋል። ከተመረጡት 12 አምባሳደሮች መካከል በኢትዮጵያ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዓመት የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ የሆነችው አሲያ ኽሊፋ ትገኛለች። ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ዓላማውን ያደረገው በዓለም ዙሪያ ያሉ ወጣት ተማሪዎችን በአጭር ጊዜ ስልጠና  የዲጂታል ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን አረዳዳቸውን ማሳደግ ነው። ለዚህም አጫጭር ስልጠናዎችን፣ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እና የተመራቂዎች ማህበር እንቅስቃሴዎች (አልሙናይ) ተሳትፎ እንዲጎለብት ይሰራል። የባህል ልውውጦች አስፈላጊነት እና የስራ ፈጣሪነት…
Read More