ዜና

በአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ሁለት ”የጦር ጄቶች እጅግ ዝቅ ብለዉ በረሩ፡፡

በአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ሁለት ”የጦር ጄቶች እጅግ ዝቅ ብለዉ በረሩ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እኩለ ቀን 6 ሰዓት አካባቢ ” ሁለት ተዋጊ የጦር ጄቶች ” ዝቅ ብለው መብረራቸውን አሻም ተመልክታለች፡፡ አሻም ጉዳዩን ለማጣራት የመከላከያ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነን አነጋግራለች፡፡ኮሎኔል ጌትነት ” የጦር ጄቶች ዝቅ ብለው መብረራቸውን ” አረጋግጠው፣ ” የጦር ጄቶቹ ዝቅ ብለው የበረሩት ልምምድ እየተደረገ ስለሆነ” ነው ብለዋል፡፡ ”በመጪው የአድዋ ድል በዓል ደግሞ የጦር ጄቶች በስፋት ትዕይንት እንደሚያሳዩ”ም ተገልጿል፡፡ የጦር ልምምዱ እስካሁን የተደረገው ብቻ ነው ወይስ ቀኑን ሙሉ ይቀጥላል” ስትል ላነሳችላቸው ጥያቄ ” ይህ ምስጢር ነው፤ ነገር ግን ሁሉም ሰላም ነው፡፡” ሲሉ መልሰዋል፡፡
Read More
አረብ ኢምሬት ለ273 ኢትዮጵያዊያን ስኮላርሺፕ ሰጠች

አረብ ኢምሬት ለ273 ኢትዮጵያዊያን ስኮላርሺፕ ሰጠች

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ሙሉ ስኮላርሺፕ መስጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው ከግማሽ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች ውስጥ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች እውቅና በሰጡበት ወቅት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተማሪዎቹ " እንኳን ደስ ያላችሁ " ካሉ በኋላ የተሰጣቸውን ፈተና በአግባቡ መስራት በመቻላቸው " ኢትዮጵያን የሚያግዙ 273 ተማሪዎች ተገኝተዋል በዚህም ደስታ ይሰማናል" ብለዋል፡፡ ተማሪዎቹ እጅግ ዘመናዊ በሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉና ለኢትዮጵያ እና አፍሪካ የሚደርሱ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ተማሪዎቹ በርትተው ተምረው ሀገራቸውን ሳይረሱ የሚጠቅሙ እንዲሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል። ሁሉም ተማሪ ጥበብን እንዲሻ…
Read More
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ከተማዎች እንደ አዲስ እንዲደራጁ ውሳኔ አሳለፈ

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ከተማዎች እንደ አዲስ እንዲደራጁ ውሳኔ አሳለፈ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 3ኛ መደበኛ 6ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ ዓመት ስብሰባ በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ከተማዎች እንደ አዲስ እንዲደራጁ ውሳኔ አሳልፏል። የአሮሚያ ክልል መንግሥት የክልሉን ሕዝብ ኑሮ እና ተጠቃሚነት በመሠረታዊነት ለማሻሻል የሚያስችሉ ፈጣን፣ ዘላቂ እና ሰፊ መሠረት ያለው ልማት በማስመዝገብ የተለያዩ የልማት ስትራጂዎችን በማመንጨት ስትራቴጂዎቹን ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ አደረጃጀቶችንና አሠራሮችን በመዘርጋት ሲሠራ መቆየቱን የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውሷል። ባለፉት ዓመታት ውስጥ የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የከተማ ልማት ለማካሄድ በከተመዎቹ የዕድገት ደረጃ መሠረት በርካታ ከተሞችን በመመሥረት ሰፋፊ ሥራዎች የተሰሩ ቢሆንም አሁን በተደረበት የዕድገት ደረጃ ዘመናዊ እና ተወዳዳሪ በመሆን ሕዝቡን እና ክልሉን የሚመጥኑ ከተሞችን ለመፍጠር እንዲሁም ሕገ-ወጥነትን…
Read More
በሱሉልታ ከተማ ቤታቸዉ የፈረሰባቸዉ ዜጎች ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገናል አሉ።

በሱሉልታ ከተማ ቤታቸዉ የፈረሰባቸዉ ዜጎች ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገናል አሉ።

በኦሮሚያ ክልል አዲስ በተቋቋመዉ በሸገር ከተማ አስተዳደር ሱሉልታ ከተማ ልዩ ስሙ ቀርዮ የተሰኘዉ ነዋሪዎች ቤታቸዉ እየፈረሰባቸዉ እንደሆነ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡ ነዋሪዎቹ መኖሪያ ቤታቸዉ ድንገት ስለሚፈርስባቸዉ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸዉን ለጣቢያችን ገልፀዋል፡፡ ቤቶቹ ያለምን ማስጠንቀቂያ ድንገት በሌሊት ጭምር እየፈረሱ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎቹ “እቃችንን እንኳን ለማንሳት ጊዜ አልተሰጠንም” ብለዋል፡፡ ቤቶቹን ማፍረስ ብቻም ሳይሆን የቤት ክዳን ቆርቆሮና በር ጨምር እየተወሰደበናቸዉ እንደሆነም ሰምተናል፡፡አሁን ላይ ቤት የፈረሰባቸዉ ዜጎች ጊዚያዊ ማረፊያ አጥተዉ ሜዳ ላይ እንደሚገኙ የገለፁት ነዋሪዎቹ ፤ ግማሾቹም ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እየተሰደዱ ነዉ ተብሏል፡፡ “ቤቶቹ ህገወጥ ሆነዉ ቢገኙ እንኳን እንድናፈረስና ለቀን እንድንወጣ ጊዜ መሰጠጥ ነበረበት” የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ መንግስት ይድረስልን ሲሉ ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ…
Read More
ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በቦረና በድርቅ ለተጎዱ 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በቦረና በድርቅ ለተጎዱ 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ለዘንድሮ የዓድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ለቦረና ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ የሚውል 1,000,000.00 (አንድ ሚልየን) ብር ለግሷል። በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ከ800 ሺህ በላይ ዜጎች በድርቅ መጎዳታቸው ሲታወስ ከ3 ሚሊዮን በላይ የቤት እንስሳትም ሞተዋል፡፡ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ የዘንድሮን የዓድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በድርቅ ሳቢያ አስቸኳይ እርዳታ ለሚፈልገው የቦረና ሕዝባችን የ1ሚልየን ብር ድጋፍ አድርጓል። በቦረና ዞን ለተከታታይ ለስድስተኛ ጊዜ ዝና ብ አለመዝነቡን ተከትሎ በድርቁ የተጎዱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን የዞኑ አስተዳድር አስታውቋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር 100 ሚሊዮን ብር በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ሰዎች ድጋፍ ሲያደርግ ሌሎችም የመንግስት እና የግል ተቋማትም ድጋፍ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል፡፡ በኢትዮጵያ…
Read More