ዜና

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 62 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለጸ።

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 62 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለጸ።

በስመኝሽ ገብረወልድ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ 43.3 በመቶ ወይም 18.9 ቢሊዮን ብር እድገት አሳይቷል ብሏል። ገቢውም የእቅዱን 90.7 መሆኑን ተናግሯል። በዘንድሮ የበጀት ዓመት ስድስት ወር ውስጥ ምንም አይነት የሳይበር ጥቃት አልደረሰብኝም ነው ያለው። በዚሁ የስራ አፈፃፀም የግዜ ማዕቀፍ 6 ሚሊዮን ገደማ ደንበኞች አፍርቻለሁ ያለው ኩባንያው በአጠቃላይ የደንበኞቼ ቁጥርም 80.5 ሚሊየን ደርሰዋል ተብሏል። ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌኮም አገልግሎት ብዛት ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም ደግሞ 17ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን ዓለም አቀፉ የቴሌኮም አገልግሎት ድርጅት ወይም ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ (GSMA) ጥናት ተረጋግጧል ተብሏል። የደንበኛን ቁጥር ለመጨመር ከተሰሩት ስራዎች መካከል በግማሽ አመቱ 202 አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎች ተጠናቀው ወደ እንደገቡም ተገልጿል። በሞባይል ኔትዎርክ በተከናወኑ የፕሮጀክት…
Read More
መንግስት በዩኤስኤይድ ጉዳይ የዲፕሎማሲ ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

መንግስት በዩኤስኤይድ ጉዳይ የዲፕሎማሲ ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

መንግስት በዩኤስኤይድ ጉዳይ የዲፕሎማሲ ድጋፍ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጠየቀ፡፡ ከአንድ ወር በፊት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ወደ ስልጣን የመጡት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ የረድኤት ድርጅት ወይም ዩኤስኤይድ ከአስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታዎች ውጪ ሌሎች ስራዎቹን እንዳይሰራ ማገዳቸው ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎም ከድርጅቱ ድጋፍ ከሚደረግላቸው ሀገራት መካከል አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡ በኢትዮጵያ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ከዩኤስኤድ ጋር ሲሰሩ እንደነበር እና ውሳኔው ከባድ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡ ከ5 ሺህ በላይ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችን በአባልነት የያዘው የዚህ የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ አህመድ ሁሴን ለአል ዐይን እንዳሉት በዩኤስኤይድ ላይ የተላለፈው የ90 ቀናት ውሳኔ ከምንም…
Read More
ታዋቂው የጉበት ስፔሻሊስት ሐኪም በባህርዳር ተገደለ

ታዋቂው የጉበት ስፔሻሊስት ሐኪም በባህርዳር ተገደለ

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥበበ ግዮን ግቢ ስፔሻላንስድ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር ዶክተር አንዷለም ዳኘ በተተኮሰባቸው ጥይት መገዳላቸውን ተገልጿል፡፡ በአማራ ክልል የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥበበ ግዮን ግቢ ስፔሻላንስድ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር ዶክተር አንዷለም ዳኘ በተተኮሰባቸው ጥይት መገዳላቸውን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል። ለደህንነታቸው ሲባል ስሜ ከመነገር ይቆይ ያሉ አንድ የዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሰራተኛ እንዳሉት “ዶክተር አንዷለም መኪናው ውስጥ በተተኮሰበት ጥይት ተመትቶ ተገኝቷል ” ሲሉ አስረድተዋል። ተኩሱ ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃዎች በፊት በአካባቢው እንዳለፉ የገለጹት እኝሁ አካል ስለ ዶክተር አንዷለም ሲገልጹ፣ “ ከሥራ እየተመለሰ በነበረበት ወቅት ቆሸ የሚባለው ሰፈር ሲደርስ ነው ጥይት የተተኮሰበት ሲሉም…
Read More
2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና አዛን ውድድር ተጠናቀቀ

2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና አዛን ውድድር ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነት በዘይድ ኢብኑ ሳቢት የቁርአን ማህበር አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን የማጠቃሊያ ውድድር በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዷል። በማጠቃሊያ ውድድሩ በቁርዓን ሂፍዝ፣ በቁርዓን ቲላዋ እና በአዛን ዘርፍ አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች በዳኞች አማካኝነት ይፋ ሆነዋል። በዚህም በወንዶች የቁርአን ሂፍዝ ውድድር 1ኛ. ሙሐመድ ፉዓድ ከሊቢያ 2ኛ. ዩሱፍ አሺር … ከኳታር 3ኛ. አህመድ በሺር …ከአሜሪካ በሴቶች የቁርአን ሂፍዝ ውድድር 1ኛ ሩቅያ ሳላህ … ከየመን 2ኛ ነሲም ጀናዉጃ … አልጄሪያ 3ኛ ቀመራ ወሊዩ መሐመድ … ከኢትዮጵያ እንዲኁም በአዛን ውድድር 1ኛ ሙሀመድሻን አቡበከር … ከኢንዶኖዢያ 2ኛ ኡመር ዱራን … ከቱርክ 3ኛ አደም ጅብሪል ……
Read More
በትግራይ ዳግም ጦርነት ይቀሰቀሳል በሚል ነዋሪዎች ገንዘብ እና ምግብ ማከማቸት ጀምረዋል ተባለ

በትግራይ ዳግም ጦርነት ይቀሰቀሳል በሚል ነዋሪዎች ገንዘብ እና ምግብ ማከማቸት ጀምረዋል ተባለ

በትግራይ ዜጎች ዳግመኛ ግጭት ይቀሰቀሳል በሚል ስጋት ባለፉት ሶስት ቀናት ዉስጥ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ሸመታ ላይ ናቸዉ ተብሏል፡፡ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ክንፍ የተሾሙ የተባሉ ግለሰብ በሚሊሻዎች ታጅበው ትናንት የመቐለ 104 ነጥብ 4 ኤፍኤም ሬድዮ ጣብያ ለመቆጣጠር መሞከራቸው ተከትሎ በሬድዮ ጣብያው ውዝግብ ተፈጥሮ ነበር። ታጣቂዎቹ ከዚህ ቀደም በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተሾሙትን የጣቢያው ሃላፊ አውርደው በሌላ ሰው የመተካት እንቅስቃሴ ማድረጋቸውንና የከተማዋ ፖሊስ ደርሶ ድርጊቱን ማስቆሙ ታውቋል። የወታደራዊ አመራሮቹ ውሳኔ ተከትሎ ደግሞ ግጭት እንዳይነሳ የሰጉ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ገንዘባቸው ከባንክ ማውጣት እና ሸቀጦች መግዛት ላይ ተጠምደዋል መባሉን ዶቼ ቬለ ዘግቧል። ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመቐለ…
Read More
ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ሀይሉን ባልሆነ ቦታ እያባከነ ይሆን?

ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ሀይሉን ባልሆነ ቦታ እያባከነ ይሆን?

የኢትዮጵያ ሐገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሁሉን አቀፍ የሆነ ብሔራዊ ምክክር ለማድረግና ከዚህ በፊት ይነሱ  የነበሩ ትርክቶች መቋጫ እንዲያገኙ በሚል ነበር በ2014 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተቋቁሞ ስራ የጀመረው፡፡ በዚህም ባለፉት ሶስት ዓመታት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ገብቶ የአጀንዳ መለየትና ሌሎች እንቅስቃሴዎችንም በመስራት ላይ ይገኛል። ኮሚሽኑ ባለፉት ዓመታት አዲስ አበባን ጨምሮ በሲዳማ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሊ፣ አፋር፣ጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ደቡብ ምዕራብ ፣ ኦሮሚያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች አጀንዳዎችን መለየቱን አስታውቋል፡፡ ይህን ተከትሎ ኢትዮ ነጋሪ የሲዳማ ክልል የሕብረተሰብ ክፍሎች በአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ላይ ያላቸውን ዕምነት እና በኮሚሽኑ በአጀንዳነት እንዲካተት ስለሚፈልጓቸው ጉዳዮች ዙሪያ ቃለ መጠይቅ አድርጓል፡፡ የ19 ዓመቷ ተማሪ ምህረት ከበደ የሐዋሳ ከተማ ነዋሪ ስትሆን ሐገራዊ ምክክር ኮሚሽን…
Read More
ቀሲስ በላይ መኮንን በ5 ዓመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ተቀጡ

ቀሲስ በላይ መኮንን በ5 ዓመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ተቀጡ

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን መዝገብ ላይ የቀረቡ የግራ ቀኝ ማስረጃዎችን መርምሮ በዛሬው የችሎት ቀጠሮ በጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወሰነ። የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ቀሲስ በላይ መኮንን፣ በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው እያሱ እንዳለ፣ በኮሚሽን ስራ ላይ የተሰማራው በረከት ሙላቱ እና አለምገና ሳሙኤል እንዲሁም የኒሞና ንግድ ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አበራ መርጋ በተባሉ ተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ ቁጥር 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና የሙስና ወንጀሎች ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 2 እና ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ…
Read More
አቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን እንዲመሩ ተሾሙ

አቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን እንዲመሩ ተሾሙ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስተዳድር ወቅት ሚኒስትር የነበሩት አቶ ብርሃኑ አዴሎ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርጎ ሾሟል፡፡ አቶ ብርሃኑ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የስልጣን ዘመን የካቤኔ ጉዳዮች ኃላፊ የነበሩ ሲሆን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን በዋና ኮሚሽነርነት ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት እንዲመሩ ተሾመዋል። ኢሰመኮን ላለፉት አምስት ዓመታት ሲመሩ የቆዩት ደናኤል በቀለ (ዶ/ር) በመተካት ሲሆን ተቋሙ ላለፉት ስድስት ወራት በተጠባባቂ ኮሚሽነር ሲመራ ቆይቷል። ዶ/ር ዳንኤል ባለፈው አመት ሐምሌ ወር የስራ ዘመናቸው ተጠናቆ ከኃላፊነታቸው ከተሰናበቱ ወዲህ የእርሳቸው ምክትል የነበሩት ራኬብ መሰለ፣ ኢሰመኮን የመምራት ኃላፊነት በተጠባባቂነት ተረክበው ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወሳል። ተቋሙ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጀምሮ በሀገሪቱ የተካሄዱ የሰብዓዊ…
Read More
አምንስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ላይ ዓለም አቀፍ ጫና እንዲደረግ ጠየቀ

አምንስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ላይ ዓለም አቀፍ ጫና እንዲደረግ ጠየቀ

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ አማራ ክልል እየተፈጸመ ነው ያለውን የጅምላ እስራት ለማስቆም አስቸኳይ አለም አቀፍ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርቧል። ድርጅቱ የሀገሪቱ መንግስት በክልሉ ሰፊ የእስር ዘመቻ ከጀመረበት መስከረም 2024 ጀምሮ አራት ወራት መቆጠራቸውን አመላክቷል፡፡ አምነስቲ ባወጣው መግለጫ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 28 ቀን 2024 የኢትዮጵያ ፌዴራል እና የአማራ ክልል የጸጥታ ሃይሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦችን ወደ አራት የጅምላ እስር ቤቶች በማጓጓዝ በክልሉ ውስጥ ማሰራቸውን ገልጿል። እስር ከተፈጸመባቸው መካከል ዳኞች፣ አቃቤ ህጎች፣ ፖለቲከኞች እና ምሁራንን ጨምሮ የፍትህ አካላት ይገኙበታል ተብሏል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ቲጌሬ ቻጉታህ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለጉዳዩ የሰጠውን ትኩረት ማነስ ተችተዋል፡፡ ዳይሬክተሩ "በአማራ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዘፈቀደ…
Read More
በአማራ ክልል በጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት 100 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተባለ

በአማራ ክልል በጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት 100 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተባለ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አንዳስታወቀው ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ አሁን በክልሉ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት በርካታ ትምህርት ቤቶች ተጎድተዋል። ለአብነትም በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከ400 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ቢሮው ጠቅሷል። በአጠቃላይ በክልሉ ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች ወደ አገልግሎት ለመመለስ 112 ቢሊየን ብር ያስፈልጋልም ተብሏል። ቢሮው ባስጠናው ጥናት መሠረት ይህ ገንዘብ ትምህርት ቤቶችን ከመገንባትና መጠገን በተጨማሪ ተጓዳኝ የትምህርት ሥራዎችን ለማከናወን የሚውል ነው፡፡ የፌደራል መንግሥት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ አደራጃለሁ ካለበት ሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል በመንግስት እና ፋኖ ታጣቂዎች የተጀመረው ጦርነት እንደቀጠለ ይገኛል። በዚህ ጦርነት ምክንያት ከስድስት ሚሊዮን በላይ ህጻናት ከትምህርት ውጪ እንደሆኑም ተገልጿል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)…
Read More