14
Apr
ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ ይዘው እንዳይሄዱ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል መጀመሩን የትምህርት ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል። ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ የሚባል ነገር ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በሚመሩት የትምህርት ዘርፍ ላይ ስለ አፈጻጻምና ስለታቀዱ እቅዶች ማብራሪያ ሰጥተዋል። በሰጡት ማብራሪያም በሚቀጥለው ሳምንት ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር ውይይት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል። በዚህም ወቅት ተማሪዎች ስልክ ትምህርት ቤት ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ ስለሚደረገው እንቅስቃሴ እንደሚመከር ገልጸዋል። “ የጋራ ስምምነት ላይ ከደረስን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርት መከታተል ነው እንጂ ከስልክ ጋር የሚጫወቱበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ይደረጋል “ ብለዋል። ብተያያዘ ዜና ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ…