Schools

በሰሜን ኢትዮጵያ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ከትምህርት ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

በሰሜን ኢትዮጵያ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ከትምህርት ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት ለማስቆም በያዝነው ዓመት ሕዳር ወር የሰላም ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል፡፡ ይሁንና የሰላም ስምምነት ቢፈረምም ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ የሕፃናት አድን ድርጅት/ሴቭ ዘ ችልድረን አስታውቋል፡፡ ድርጅቱ ለኢትዮ ነጋሪ በላከው መግለጫ እንዳለው የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር ተጨማሪ የገንዘብ እርዳታ ያስፈልጋል ብሏል፡፡  በአሁኑ ወቅት በመላው ኢትዮጵያ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሕፃናት በላይ ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን ይህም እድሜያቸው ለትምህርት ከደረሰ 16 ኢትዮጵያውያን ሕፃናት መሃከል አንዱ ከትምህርት ገበታ መገለሉን ያሳያል ተብሏል፡፡ ይህ አሃዝ ኢትዮጵያን ከትምህርት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቀውስ ካስተናገዱ ሃገራት አንዷ እንደሚያደርጋት ተገልጿል፡፡  በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልል ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች በሚገኙ…
Read More