09
Oct
1ሺህ 328 ትምህርት ቤቶች ደግሞ አንድም ተማሪ እንዳላሳለፉ ተገልጿል።በ2015 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ 845 ሺሕ 099 ተማሪዎች ውስጥ፤ 817 ሺሕ 838 ተማሪዎች ከ50 በመቶ በታች የሆነ ውጤት ማምጣታቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ ከአጠቃላይ 845 ሺሕ 099 ተፈታኞች ውስጥ 27 ሺሕ 267 ተማሪዎች ወይንም (ሦስት ነጥብ ኹለት በመቶ ብቻ) 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት አምጥተዋል። በተፈጥሮ ሳይንስ ከተፈተኑ 356 ሺሕ 878 ተማሪዎች ውስጥ 19 ሺሕ 017 ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ሲመጡ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከተፈተኑ 488 ሺሕ 221 ተማሪዎች ውስጥ 7…