Nationalexam

ስድስት ዩንቨርሲቲዎች የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎችን እንደማይቀበሉ ተገለጸ

ስድስት ዩንቨርሲቲዎች የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎችን እንደማይቀበሉ ተገለጸ

ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከግማሽ በላይ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎችን እንደሚመድብ ገልጿል፡፡ ይሁንና ስድስት የመንግስት ዩንቨርሲቲዎች የሬሚዲያል ተማሪዎችን እንደማይቀበሉ አስታውቋል፡፡ የሬሚዲያል ተማሪዎችን ከማይቀበሉ ዩንቨርሲቲዎች መካከልም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ አርሲ ዩኒቨርሲቲ እና ኮተቤ የትምህርት ዪኒቨርሲቲዎች ናቸው፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር እነዚህ ዩንቨርሲቲዎች ለምን የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎችን እንደማይቀበሉ ምክንያታቸውን አልጠቀሰም፡፡ በ2015 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ 845 ሺሕ 099 ተማሪዎች ውስጥ፤ 817 ሺሕ 838 ተማሪዎች ከ50 በመቶ በታች የሆነ ውጤት ማምጣታቸው ይታወሳል፡፡ የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ ከአጠቃላይ 845 ሺሕ 099 ተፈታኞች ውስጥ…
Read More
ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውስጥ 817 ሺህ ተማሪዎች መውደቃቸው ተገለጸ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውስጥ 817 ሺህ ተማሪዎች መውደቃቸው ተገለጸ

1ሺህ 328 ትምህርት ቤቶች ደግሞ አንድም ተማሪ እንዳላሳለፉ ተገልጿል።በ2015 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ 845 ሺሕ 099 ተማሪዎች ውስጥ፤ 817 ሺሕ 838 ተማሪዎች ከ50 በመቶ በታች የሆነ ውጤት ማምጣታቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የ2015  የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ ከአጠቃላይ 845 ሺሕ 099 ተፈታኞች ውስጥ 27 ሺሕ 267 ተማሪዎች ወይንም (ሦስት ነጥብ ኹለት በመቶ ብቻ) 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት አምጥተዋል። በተፈጥሮ ሳይንስ ከተፈተኑ 356 ሺሕ 878 ተማሪዎች ውስጥ 19 ሺሕ 017 ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ሲመጡ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከተፈተኑ 488 ሺሕ 221 ተማሪዎች ውስጥ 7…
Read More
በአዲስ አበባ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች በቡድን መደባደባቸው ተገለጸ

በአዲስ አበባ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች በቡድን መደባደባቸው ተገለጸ

በአዲስ አበባ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች በቡድን መደባደባቸው ተገለጸ በጎንደር ዩኒቨርስቲ የ12ተኛ ክፍል ፈተና ፈታኝ እና ሁለት ፖሊሶች መገደላቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል የ12ኛ ክፍል ፈተናን ለመፈተን ከአዲስ አበባ ከተማ ካሉ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ወደ ዩንቨርሲቲ የመጡ ተማሪዎች በቡድን መደባደባቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ላይ እንዳሉት በትምህር ቤቶቻቸው በመቧደን ተደባድበዋል ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የዶርም በር፣ ሎከር እና ሌሎች አካላዊ ጉዳት ደርሷል ብለዋል፡፡ ፖሊስ ክስተቱን እያጣራ ነው ያሉት ሚኒስትሩ 87 ተማሪዎች ተይዘው ምርመራ በመካሄድ ላይ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለም ከአዲስ አበባ ውጪ በጎንደር እና በጋምቤላ የ12ኛ ክፍል ፈተና በተወሰነ ደረጃ መስተጓጎሉ ተገልጿል፡፡ በጎንደር በተከሰተው ግጭት ምክንያት 16 ሺህ…
Read More
ትምህርት ሚኒስቴር የሬሚዲያል ፈተናዎችን ሰረዘ

ትምህርት ሚኒስቴር የሬሚዲያል ፈተናዎችን ሰረዘ

የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ወስደው ወደ ዩንቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎችን የሬሚዲያል ፕሮግራም በመስጠት ለይ መሆኑ ይታወሳል፡፡ እነዚህ ተማሪዎች ከትናንት ሰኔ 26 ቀን ጀምሮ የ12ኛ ክፍል ፈተናን በያሉበት ሆነው በመፈተን ላይ ናቸው፡፡ ይሁንና ሚኒስቴሩ ይህ ፈተና መሰረዙን ያስታወቀ ሲሆን ምክንያቹን ከመናገር ተቆጥቧል፡፡ በፈተና ሂደት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ እንዲሁም ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ፕሮግራም ማሻሻያ እንደተደረገበትም ገልጿል፡፡ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን…
Read More