Highereducationinethiopia

ኢትዮጵያ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዳይሰጥ አገደች

ኢትዮጵያ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዳይሰጥ አገደች

በዩንቨርሲቲዎች የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት እንዳይሰጡ እገዳ ተጥሎባቸዋል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ከታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረው አሳውቋል፡፡ ከጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የነበረውንና በትግበራ ወቅት ክፍተት የታየበት "የአካዳሚክ ሠራተኞች የደረጃ ዕድገት መመሪያ" በመሻሻል ላይ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡ በዚህም ማሻሻያው ተጠናቆ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እስከሚላክ ድረስ በሁሉም ተቋማት የፕሮፌሰርነት ዕድገት አሰጣጥ ለጊዜው መታገዱን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡ ይሁን እንጂ "አንዳንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክልከላውን በመጣስ፣ መመሪያውን ባልተከተለ፣ ግልጽነት በጎደለው፣ ወጥነት በሌለው እና ከትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ሪፎርሞች ጋር በሚጣረስ መልኩ የፕሮፌሰርነት ዕድገት መስጠት እንደቀጠሉ የትምህርት ሚኒስትር…
Read More