27
Nov
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን በሲቪል ማህበረሰብ ስራዎች ዙሪያ የተሰማሩ ድርጅቶችን ማሸጉ ይታወሳል፡፡ ከታገዱት ድርጅቶች መካከልም “የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል” (CARD) “ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ” (AHRE) እና ሌሎችም ይገኙበታል። ባለሥልጣኑ ለድርጅቶቹን ያገደው በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ጣልቃ ገብተዋል በሚል ነበር፡፡ አለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪው አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የጣለውን እገዳ አውግዟል፡፡ የመብቶች እና የዲሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ)፣ ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ እና የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች የተሰኙት ድርጅቶች ላይ የተጣለው እገዳ በሲቪል ማኅበረሰቡ ምኅዳር ላይ የተቃጣው አፈና እየጨመረ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ሲልም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ ላይ ጠቅሷል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ እና ደቡባዊ…