ECSOC

መንግስት በዩኤስኤይድ ጉዳይ የዲፕሎማሲ ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

መንግስት በዩኤስኤይድ ጉዳይ የዲፕሎማሲ ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

መንግስት በዩኤስኤይድ ጉዳይ የዲፕሎማሲ ድጋፍ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጠየቀ፡፡ ከአንድ ወር በፊት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ወደ ስልጣን የመጡት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ የረድኤት ድርጅት ወይም ዩኤስኤይድ ከአስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታዎች ውጪ ሌሎች ስራዎቹን እንዳይሰራ ማገዳቸው ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎም ከድርጅቱ ድጋፍ ከሚደረግላቸው ሀገራት መካከል አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡ በኢትዮጵያ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ከዩኤስኤድ ጋር ሲሰሩ እንደነበር እና ውሳኔው ከባድ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡ ከ5 ሺህ በላይ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችን በአባልነት የያዘው የዚህ የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ አህመድ ሁሴን ለአል ዐይን እንዳሉት በዩኤስኤይድ ላይ የተላለፈው የ90 ቀናት ውሳኔ ከምንም…
Read More