04
Mar
በሀገራችን ኢትዮጵያ ተሰባስቦ ተረዳድዶና ተደጋግፎ መኖር በአጠቃላይ ማህበራዊ ሕይወት አንዱ የሕይወት ዑደት ነው። ታዲያ ይህ የመረዳዳት ሒደት ደስታን ሐዘንን እንዲሁም የጤና እክልን መሠረት በማድረግ የሚከወን ነው በተለይም እድር እና እቁብን እንደ ምሳሌ ብንወስድ ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ የሚባሉ እና ማህበረሰቡ ጠብቆና አክብሮ የያዛቸው መረዳጃ እና መደጋገፊያ ሕብረቶችናቸው። ታዲያ እነዚህ ሕብረቶች በአንድም በሌላም መልኩ እክል ሲገጥማቸው አሊያም የመፍረስ አደጋ ሲጋረጥባቸው ለመታደግ ጊዜ የሚፈጅ እና አስቸጋሪ ይሆናል። በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ከዛም በፊት በነበረው የኮሮና ወረርሺኝ እንዲህ ያሉ መረዳጃ ማህበራትን ለማጥፋት አሊያም ለማቀዝቀዝ ዋነኛ ምክንያቶች ሆነዋል። በመቀሌ ከተማ የሚገኝ ትልቅ እድር ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ለተኪዳን በነዚህ ሁለት አጋጣሚዎች የተፈጠረውን የእድሩን ከፍተኛ መቀዛቀዝ ሲገልጹ…