Factchecking

መቐለ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥለው ሳምንት ሥራ ይጀምራል መባሉን አስተባበለ

መቐለ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥለው ሳምንት ሥራ ይጀምራል መባሉን አስተባበለ

መቐለ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥለው ሳምንት ሥራ ይጀምራል በሚል የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀበሰሜን ኢትዮጵያ ሲካሄድ በነበረው ጦርነት ምክንያት የመማር ማስተማር ሥራው የተቋረጠው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ሥራውን እንደሚጀምር በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲዘገብ ቆይቷል። በዚህም ዩኒቨርሲቲው በሚቀጥሉት አራት ወራት 24 ሺሕ የሚጠጉ የቀድሞ ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅ እና ከመስከረም ወር 2016 ጀምሮ አዲስ ተማሪዎችን እንደሚቀበል የተገለጸ ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲው በመንግሥት በኩል የሚያስፈልግ በጀት ሁሉ እንደተለቀቀለትም ተነግሯል። ነገር ግን ይህ መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የዩኒቨርስቲው ሰራተኞች እና አመራሮች አረጋግጠዋል። መቐለ ዩኒቨርሲቲም ይህንን ዜና የሚመለት መረጃ በይፋዊ የፌስቡክ እና የትዊተር አካውንቱ ላይ አላወጣም። የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋና ሓጎስ ዩኒቨርሲቲው ሥራ ለመጀመር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር…
Read More