22
Jan
ጎንደር ዩንቨርስቲ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ 100 ሺህ ተማሪዎችን እንዳስመረቀ ተገልጿል። ዩንቨርሲቲው በኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ዕጥረት ለመፍታት በሚል በ1947 ዓ.ም መመስረቱም ተገልጿል። የዩንቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አጸደወይን እንዳሉት ዩንቨርሲቲው በ70 ዓመት ታሪኩ 100 ሺህ ተማሪዎችን አሰልጥኖ አስመርቋል ብለዋል። በኢትዮጵያ የሐኪሞች ዕጥረትን ተከትሎ የውጭ ሀገራት የህክምና ባለሙያዎች ወደ ሀገር ውስጥ ይገቡ ይነበረ ሲሆን ጎንደር ዩንቨርሲቲ ይህ ችግር በቋሚነት እንዲፈታ የራሱን አስተዋጽኦ መወጣቱም ተጠቅሷል። ጎንደር ዩኒቨርስቲ ሕንፃ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገነባ መሬታቸውን ለሰጡ ግለሰቦች ዕውቅና በመስጠት የአርሶ አደሮች ቀንን እሰይማለሁም ብሏል። በተመሳሳይ በተለያየ መንገድ አሰተዋፅኦ ላደረጉለት ግለሰቦች የሕንፃ፣ የመንገድና የአዳራሽ ስያሜ ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል። ፕሬዚዳንቱ በመግለጫቸው ስያሜው በዩኒቨርስቲውና በሆስፒታሉ ታሪክ ጉልህ ድርሻ ለነበራቸው ግለሰቦች፣…