21
Nov
በሽታው በንክኪ የሚተላለፍ በመሆኑ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰባቸው እንደማይሰጥ ተገልጿል። ህይወታቸው ካለፈ በኋላ አስከሬኑ የማይታጠብ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ የቀብር ስርዓታቸው ይፈፀማል ተብሏል። ቀብር የተፈፀመባቸው ቦታዎችም በደንብ መጠበቅ እንዳለባቸው ተገልጿል። ማህበረሰቡ የበሽታውን ከባድነት ተረድቶ ይህንን ውሳኔ መቀበል እና መተባበር አለበት ተብሏል። በሌላ በኩል ቫይረሱ በወንድ የዘር ፈሳሽ ውስጥ ለአንድ አመት ጊዜ የሚቆይ በመሆኑ ፥ ከህመሙ ያገገሙ ሰዎች ልቅ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት ከማድረግ መቆጠብ አለባቸው ነው የተባለው። ተገቢው ክትትል እና ህክምና ተደርጎለት የዳነ ሰው በሽታውን ማስተላለፍ አይችልም። እንደ ኮሮና ቫይረስ በአየር ይተላለፋል የሚል የተዛባ አመለካከት መኖሩ የተገለፀ ሲሆን፥ ህመሙ በአየር የማይተላለፍ ነው ተብሏል። ህመሙ በንክኪ የሚተላለፍ በመሆኑ ህመሙ…