29
Oct
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ የአምስት ሚንስትሮችን ሹመት ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውሳኔ አሳልፏል። ለምክር ቤቱ ከቀረቡ አጀንዳዎች መካከል የአምስት ሚንስትሮች ሹመት አንዱ ሲሆን የምክር ቤት አባላት እና የመንግስት ተጠሪ ክርክር አድርገዋል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሁለት ሳምንታት በፊት የሾሟቸው አምስት ሚንስትሮች በዛሬው የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የቀረበ ሲሆን የምክር ቤት አባላት በሹመቱ ዙሪያ ጥያቄ አንስተዋል። ከተነሱ ጥያቄዎች መካከልም የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ተደርገው የተሾሙት እና ስራ የጀመሩት ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) አንዱ ነበር። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ወክለው የምክር ቤቱ አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ጥያቄ ካነሱት መካከል አንዱ ነበሩ። ሹመቱን አስመልክቶ ካነሱት ጥያቄ መካከልም "የፍትህ…