ኢኮኖሚ

ኢትዮጵያ በሶስት ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በሶስት ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር እንደገለጸው ባለፉት ሦስት ወራት ለውጭ ገበያ ካቀረበቻቸው ምርቶች 2 ነጥብ 48 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን አስታውቋል። ሚንስቴሩ በበጀት ዓመቱ ሩብ ወራት ጥራጥሬንና የቅባት እህሎችን ከመሳሰሉ ምርቶች 149 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን ገልጿል። በተያዘው በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ ዘርፉ ለማግኘት የታቀደው አጠቃላይ ገቢ 9 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ይህም ባለፈው በጀት ዓመት ከተገኘው ገቢ የ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ብልጫ አለው። ከፍተኛ ገቢ ካስገኙ ምርቶች መካከል ቡና ሲሆን 762 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገልጿል። ገቢው የተገኘው፣ 113 ሺህ 542 ቶን ቡና በመላክ ነው የተባለ ሲሆን ከ151 ሺሕ 969 ቶን በላይ ቡና በመላክ፣ 622 ነጥብ 5…
Read More
ኢትዮጵያ ስታካሂደው የነበረው የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ዕዳ ድርድር ተቋረጠ

ኢትዮጵያ ስታካሂደው የነበረው የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ዕዳ ድርድር ተቋረጠ

ኢትዮጵያ የ 1 ቢሊዮን ዶላር የቦንድ ዕዳዋን ለማዋቀር ስታደርግ የነበረዉ ድርድር ያለ ስምምነት ተጠናቀቀ። የኢትዮጵያ መንግሥት በ2024 ዓ.ም. ዋናው ዕዳ የሚከፈልበት የአንድ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ቦንድ ዕዳዋን ለማዋቀር  ያደረገው ወሳኝ ጥረት ከቦንድ ባለቤቶች ተወካዮች ጋር ሲያደርገው የነበረው ድርድር ያለ ስምምነት መጠናቀቁ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ለዚህ ብድር በየዓመቱ 6.625% ወለድ ለመክፈል መስማማቷ ይታወቃል። የገንዘብ ሚኒስትር እንዳስታወቀው በመስከረም 15 እና ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም መካከል የተካሄደው ውይይት በሁለቱ ወገኖች የቀረቡትን የመጨረሻ የዕዳ ማዋቀር ሃሳቦች መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ አልተቻለም። ሚኒስቴሩ ድርድሩ በዚህ ጊዜ ሳይሳካ ቢቀርም፣ "ሰፊ መሻሻል" መመዝገቡን ገልጾ፣ ውይይቱ ወደፊት እንደሚቀጥል ተስፋውን አጠናክሯል። ሁለቱም ወገኖች ለአዲሱ ቦንድ እትም ዋናውን ዕዳ በ15%…
Read More
ታርኮ አቪዬሽን ከፖርቱ ሱዳን- አዲስ አበባ የቀጥታ በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

ታርኮ አቪዬሽን ከፖርቱ ሱዳን- አዲስ አበባ የቀጥታ በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

ታርኮ አቪዬሽን የተሰኘው ተቋም ከሱዳን ጊዜያዊ የአስተዳድር ዋና ከተማ ከሆነችው ፖርቱ ሱዳን ወደ አዲስ አበባ የቀጥታ በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል። የቀጥታ በረራው ከጥቅምት 20 ጀምሮ እንደሚጀመር የኩባንያው ክልላዊ ስራ አስኪያጅ ኦማር አህመድ እድሪስ ገልጸዋል። እንደ ኦማር አህመድ ገለጻ የታርኮ አቪዬሽን ቀጥታ በረራ መጀመር የኩባንያው አድማሱን ለማስፋት የያዘው እቅድ ነው። የቀጥታ በረራው በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ያለውን የንግድ ትብብር ከመጨመሩ ባለፈ ለነጋዴዎች፣ ኢንቨስተሮች እና ተጓዦችም ልዩ እድል እንደሚሰጥ ተገልጿል። ታርኮ አቪዬሽን ከፖርት ሱዳን- አስመራ የቀጥታ በረራ ያለው ሲሆን አዲሱ ከፖርት ሱዳን- አዲስ አበባ የቀጥታ በረራ የኩባንያውን ተደራሽነት ያሰፈዋልም ተብሏል። ስራ አስኪያጁ አክለውም ታርኮ አቪዬሽን ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት እና ደህንነት ዋነኛ ትኩረቶች…
Read More
የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ከ2 ቢሊዮን በላይ ብር አረቦን ሰበሰበ

የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ከ2 ቢሊዮን በላይ ብር አረቦን ሰበሰበ

ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 2 ነጥብ 08 ቢሊዮን አረቦን ብር መሰብሰቡን የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ገለጸ። መድን ፈንዱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከተው፤ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ውስጥ 2 ነጥብ 08 ቢሊዮን አረቦን ብር እንደሰበሰበና ይህም ከታቀደው እቅድ አንጻር መቶ በመቶ ተፈጻሚ ሆኗል። ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲታይም የ27 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጿል። የተሰበሰበው አረቦን ብር ሊያድግ የቻለው የአባል ፋይናንስ ተቋማት ተቀማጭ ገንዘብ በማደጉ ምክንያት እንደሆነም ተጠቅሷል። በ2018 በጀት ዓመት በአጠቃላይ ብር 9 ነጥብ 56 ቢሊዮን ከአባል ፋይናንስ ተቋማት ለመሰብሰብ ዕቅድ ይዞ እየሠራ እንደሚገኝና ይህም ከ2017 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ30 ነጥብ 25 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጿል። የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን…
Read More
ኢትዮጵያ ከውጭ እርዳታ የምታገኘው ገቢ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ከውጭ እርዳታ የምታገኘው ገቢ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሼን ባለፉት  2 ዓመታት ኢትዮጵያ ከውጪ የምታገኘው እርዳታ ማሽቆልቆሉን ባደረግሁት ጥናት አረጋግጫለው ብሏል። በተለይ ከ4 ዋና ዋና አበዳሪዎች ማለትም ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ እንግሊዝ እና አሜሪካ ለተከታታይ 3 ዓመታት የተገኘው እርዳታ እንደቀነሰ በጥናቴ አረጋግጫለሁ ብሏል። በየጊዜው ለኢትዮዽያ ኢኮኖሚ የሚበጀውን ሀሳብ የሚያዋጣውና የሚመክረው የኢትዮዽያ የኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ተመራማሪዎች እና አጥኝዎች ሰሞኑን በኢትዮዽያ የውጪ  እዳ ጫና እና እርዳታ መዳከም ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል። በተለይ ለኢትዮዽያ ይደረግ የነበረው የውጪ እርዳታ መቀነሱ የሚያመጣው ጫና እንዳለ በጥናቱ መብራራቱ ታውቋል። በህፃናት፣ በፋይናንስ አካታችነት፣ በወጣቶች ስራ ፈጠራ፣ በሴቶች እና ተያያዥ ጉዳዮች የተቋረጠው እርዳታ ምን ጫና አመጣ ኢትዮዽያስ ምን ማድረግ ይኖርባታል በሚለው ጉዳይ ምሁራኑ መክረዋል። አዲስ ካሳሁን (ዶ/ር) በኢትዮዽያ ኢኮኖሚክስ…
Read More
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይትን በይፋ ተቀላቀለች

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይትን በይፋ ተቀላቀለች

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይት ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡ የንግድ ማስጀመሪያው ፕሮግራሙን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ታድመዋል። ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይት የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ከማሳለጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡ የንግድና ቀጠናዊ ተስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የAfCFTA ግብይት የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ከማሳለጥ ባለፈ ለንግድ ዘርፉ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል። ከዚህ ባለፈም ለኢትዮጵያን ንግድ ዘርፍ መስፈንጠር ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስገንዝበዋል፡፡ ግብይቱ መጀመሩን አስመልክቶ ሥጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና በየብስ ትራንስፖርት አማካይነት ወደ…
Read More
ኢትዮጵያ ታማኝ ግብር ከፋዮች በቪአይፒ ኤርፖርት እንዲስተናገዱ ፈቀደች

ኢትዮጵያ ታማኝ ግብር ከፋዮች በቪአይፒ ኤርፖርት እንዲስተናገዱ ፈቀደች

ወርቅ እና ከዚያ በላይ ሽልማት ያገኙ ታማኝ ግብር ከፋዮች በቪአይፒ ኤርፖርት እንዲስተናገዱ መወሰኑ ተገልጿል። ወርቅ እና ከዚያ በላይ ሽልማት ያገኙ ታማኝ ግብር ከፋዮች በቪ.አይ.ፒ ኤርፖርት እንዲስተናገዱ መንግሥት መወሰኑን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ትናግረዋል። ላለፉት አራት አመታት በታማኝነት ፕላቲኒየም ሽልማት ያገኙ 30 ልዩ ተሸላሚዎች የኢትዮጵያ ዜጎች ከሆኑ፤ የድርጅት ባለቤቶች ወይም ሥራ አስኪያጆች ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት እንደሚሰጣቸውም ተገልጿል። ይህ የተገለጸው 7ኛው ዙር የታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና መርሃ ግብር በትናንትናው ዕለት በተካሄደበት ወቅት ሲሆን በመርሃ ግብሩ 700 የሚደርሱ ተቋማት እና አልሚ ድርጅቶች እውቅና ተሰጥቷቸዋል። በዚህም 105 የሚሆኑት በፕላቲኒየም ደረጃ፣ 245 በወርቅ ደረጃ የተቀሩት 350 የሚሆኑት ደግሞ በብር ደረጃ ዕውቅና ያገኙ ናቸው ተሰጥቷቸዋል። ከዚህ…
Read More
ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ፍትሐዊ ባልሆነ ውድድር መፈቱን የአለም ባንክ ገለጸ

ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ፍትሐዊ ባልሆነ ውድድር መፈቱን የአለም ባንክ ገለጸ

የዓለም ባንክ ባወጣው አዲስ ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ በቅርቡ የገባው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በሚደረገው ውድድር ፍትሃዊ ያልሆነ የመጫወቻ ሜዳ እንደገጠመውና ለከፍተኛ ኪሳራ እንደተዳረገ ይፋ አድርጓል። "የኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ግምገማ" በሚል ርዕስ የቀረበው ይህ ሪፖርት፣ በሁለቱ ኩባንያዎች መካከል ያለውን ያልተመጣጠነ ውድድር በዝርዝር ይተነትናል። ሪፖርቱ እንደሚለው፣ ኢትዮ ቴሌኮም እንደ ሳፋሪኮም 850 ሚሊዮን ዶላር የፈቃድ ክፍያ ባለመክፈሉና በስድስት የገበያ ዘርፎች ላይ የበላይነት ያለው ተቋም (SMP) ሆኖ በመቆጠሩ ውድድሩ ፍትሃዊ አይደለም። ኢትዮ ቴሌኮም ከደንብ አስከባሪው ከተቀመጠው የመገናኛ ዋጋ (MTR) በታች የድምጽ ጥሪ ዋጋ በማቅረቡ፣ ሳፋሪኮም ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች በሚደረግ እያንዳንዱ ጥሪ ላይ ኪሳራ እንደሚያስተናግድ ሪፖርቱ ገልጿል (በወር 1.6 ሚሊዮን ዶላር ይገመታል)።…
Read More
በኢትዮጵያ የኢንተርፕርነርሺፕ ባንክ ሊቋቋም መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የኢንተርፕርነርሺፕ ባንክ ሊቋቋም መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን በፋይናንስ ለመደገፍ 'ኢንተርፕርነርሺፕ ኢንቨስትመንት ባንክ' ሊቋቋም መሆኑ ተገልጿል። ባንኩ በ20 ሚሊዮን ዶላር መነሻ ካፒታል የሚመሰረት ሲሆን፣ ወጣቶች ለድጋፍ የሚያስይዙት ዋስትና የፈጠራ ሀሳባቸውን ብቻ እንደሚሆን ተጠቁሟል። ባንኩን ለማቋቋም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ ፊርማ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ተቋሙ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለኢንተርፕራይዞች አቅም መጎልበት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል። ይህ እርምጃ መንግስት የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያወጣቸውን ፖሊሲዎች ወደ ተግባር የመቀየር አካል መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ገልጸው፣ ባንኩ የወጣቶችን ጥያቄ በመመለስ የፈጠራ አቅማቸውን ለማጎልበት ያስችላል ብለዋል። ከመነሻ ካፒታሉ 10 ሚሊዮን ዶላር ከአፍሪካ ልማት ባንክ በድጋፍ…
Read More
ኢትዮጵያ 78 በመቶ የሬሚታንስ ገቢዋን እንደምታጣ ተገለጸ

ኢትዮጵያ 78 በመቶ የሬሚታንስ ገቢዋን እንደምታጣ ተገለጸ

ሀገሪቱ ከሬሚታንስ ገቢ 35 ቢሊዮን ዶላር ገቢ የማግኘት አቅም እንዳላት ተገልጿል ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት በሕጋዊ መንገድ ከሚላክላት ገንዘብ (ሬሚታንስ) የምታገኘው ገቢ የሀገሪቱን አቅም 22 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ በተለያዩ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች ጋር በመወያየት ላይ ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት በተባበሩት አረብ ኢምሬት እና ሳውዲ አረቢያ ከተሞች ከኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች ጋር የተወያዩት ፕሬዝዳንቱ አሁን ደግሞ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ኢትዮጵያ ከሬሚታንስ ገቢ እየተገኘች ያለው ገቢ 7.2 ቢሊየን ዶላር ብቻ ነዉ ብለዋል። አቶ አቤ ሳኖ እንዳስረዱት፣ አሁን ካለው የገንዘብ ፍሰት ቀሪው 78 በመቶ የሚሆነው ወደ ሀገር…
Read More