ዜና

ኢትዮጵያ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ ልትገነባ መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮጵያ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ ልትገነባ መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ ልትገነባ መሆኑንና ለዚህም የሚረዱ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ''የምሁራን ሚና ለሀገር ብልፅግና'' በሚል መሪ ሃሳብ በተካሄደ ውይይት ላይ እንደተናገሩት፤ በቴክኖሎጂው ዘርፍ መሽቀዳደም የግድ ይላል ብለዋል። አሁን ላይ በዓለማችን አንድ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ብቻ የሚገኝ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የሚገነባው ደግሞ የዓለማችን ሁለተኛው ይሆናል ማለታቸውንም ጋዜጣ ፕላስ ዘግቧል። ዩኒቨርሲቲው በቁጥር ጥቂት ነገር ግን ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን 1 ሺህ ተመራቂዎች ለማፍራት ያለመ መሆኑን ዐቢይ (ዶ/ር) አስረድተዋል። እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ ለሁሉም…
Read More
የቡና ግብይት ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ውጭ በስፋት እንደሚካሄድ ተገለጸ

የቡና ግብይት ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ውጭ በስፋት እንደሚካሄድ ተገለጸ

ለውጭ ገበያ የማይውሉ ና የተመለሱ ምርቶች ግብይት በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ብቻ በኩል እንዲሸጡ አስገዳጅ አሰራር ቢዘረጋም ምርቶቹ መዳረሻቸዉ እየታወቀ አይደለም ተብሏል። ከዉጪ ገበያ የሚመለሱት ምርቶች ግብይት በኢትዮጵያ ምርት ገበያ አማካኝነት መሆን እንዳለበት ቢቀመጥም ይህ ተግባራዊ እየተደረገ እንዳልሆነ ተገልጿል። የፌደራል ዋና ኦዲተር እንዳስታወቀው ቡናን ጨምሮ ሁሉም ምርቶች መዳረሻቸዉ እየታወቀ አለመሆኑን ተናግሯል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ የምርት ቅበላ፣ ክምችት እና የግብይት ሥርዓት አፈፃፀምን በተመለከተ የተከናወነ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ ማብራሪያ ጠይቋል። ከዉጪ ገበያዉ የሚመለሰዉን እና የማይወለዉን ምርት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሻጭ እና ገዥን የማገናኘት ሀላፊነት በግብይቱ ላይ እየታየ አይደለም ሲሉ የፌደራል ዋና ኦዲተር…
Read More
ህንጻዎች እና ቤቶች በጣሪያቸው ላይ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ እንዲገጥሙ ሊገደዱ ነው

ህንጻዎች እና ቤቶች በጣሪያቸው ላይ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ እንዲገጥሙ ሊገደዱ ነው

በሕንፃዎችና በቤቶች ውስጥ የፀሐይ ኃይል መጠቀምን አስገዳጅ የሚያደርግ የፖሊሲ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ያላትን የፀሐይ ኃይል በሙሉ አቅሟ ለመጠቀም የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል። በሚኒስቴሩ የኢነርጂ ልማትና መረጃ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ዳቢ፣ በሁሉም ሕንፃዎችና ቤቶች ውስጥ የፀሐይ ኃይል አጠቃቀምን በሒደት አስገዳጅ ለማድረግ የሚያስችል የፖሊሲ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ያላትን የፀሐይ ኃይል አቅም የመለየትና በምን መልኩ ጥቅም ላይ መዋል እንደሚቻል የሚያሳዩ ጥናቶች መጠናቀቃቸውንም አስረድተዋል። ከሌሎች የዓለም ሀገራት ልምድ በመውሰድ፣ በተለይም በከተሞች ረዣዥም ሕንፃዎች ባሉባቸው አካባቢዎች በእያንዳንዱ ቤትና ሕንፃ ጣሪያ ላይ የፀሐይ ኃይል ቴክኖሎጂን በመግጠም፣ ኃይል የመሰብሰብና ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል የፖሊሲ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን…
Read More
በአማራ ክልል ያለው ስደት አስደንጋጭ መሆኑ ተገለጸ

በአማራ ክልል ያለው ስደት አስደንጋጭ መሆኑ ተገለጸ

የአማራ ክልልን ለቆ ወደ ስደት እና ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚፈልሰው የክልል ተወላጅ መጠን "አጅግ አስደንጋጭ " መሆኑን የክልሉ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ። በአማራ ክልል ባለፉት 5 ወራት ወደ ትምህርት ገበታቸው የተመለሱ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች 36 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ተናግሯል። ይህ የተነገረው የትምህርት ቢሮው የክልሉ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ላይ የ5 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት እንደሆነ ሸገር ኤፍኤም ዘግቧል። የምክር ቤቱ አባላት ለተማሪዎች በትምህርት ገበታ አለመገኘት ጦርነቱን፣ ስደት፣ የቀን ስራ፣ በትምህርት ተስፋ መቁረጥን ጨምሮ የተለያዩ ምክንያቶችን ዘርዝረዋል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ወደ ትምህርት ያልተመለሱ ተማሪዎች አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንኳን መረጃ ማግኘት እንዳልተቻለ አስረድተዋል። አንድ የምክር…
Read More
ድንበር አቋርጠው የሚወጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በ38 በመቶ መጨመሩ ተገለጸ

ድንበር አቋርጠው የሚወጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በ38 በመቶ መጨመሩ ተገለጸ

​የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) የጥቅምት 2025 ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ በኢትዮጵያ በሚገኙ ስድስት የድንበር ፍሰት መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ የታየው የሰዎች እንቅስቃሴ ካለፈው መስከረም ወር ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል። በወሩ ውስጥ በአጠቃላይ 45,150 የሰዎች ዝውውር የተመዘገበ ሲሆን፣ ይህም በቀን በአማካይ 1,456 ሰዎች ድንበር እንደሚያቋርጡ ያሳያል ነው የተባለው። ከእነዚህ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አብዛኛው ማለትም 78.3 በመቶው (35,341 ሰዎች) ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ የሚወጡ ሲሆን፣ ቀሪው 21.7 በመቶው (9,809 ሰዎች) ደግሞ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ናቸው። በጥቅምት ወር ድንበር አቋርጠው የሚወጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ካለፈው የመስከረም ጋር ሲነጻጸር የ38 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ሪፖርቱ አመላክቷል። ይህ የፍልሰት መጨመር በተለይ በሱዳን ድንበር በሚገኘው በመተማ በኩል በከፍተኛ ሁኔታ የታየ…
Read More
በጋምቤላ ክልል እየተፈጸሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ኢሰመኮ አሳሰበ

በጋምቤላ ክልል እየተፈጸሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ኢሰመኮ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከኅዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ በጋምቤላ ወረዳ (አቦል)፣ በጋምቤላ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭትና የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና ሥጋቶችን እየተከታተለ መሆኑን አስታውቋል። ኢሰመኮ ባሰባሰበው መረጃ በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡመድ ኡጁሉ መገደልን ተከትሎ በከተማውና በአካባቢው ባሉት ወረዳዎችና ቀበሌዎች ግጭት ተፈጥሮ በተለያዩ አከባቢዎች የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ መቆየቱን አስታውቋል፡፡ በዚህም ሳቢያ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን፣ የሰዎችን እና የመጓጓዣ አማራጮችን እንቅስቃሴ የሚገድብ የሰዓት እላፊ በክልሉ መንግሥት መጣሉን፤ ባንኮችንና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት…
Read More
በጋምቤላ ክልል የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከለከለ

በጋምቤላ ክልል የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከለከለ

የጋምቤላ ክልል መንግሥት ባወጣው መግለጫ "ግጭት እና የሰው ሞት የሚያስደስታቸው ሀይሎች በሰሞኑ የጋምቤላ ከተማን ጨምሮ በሌሎች ወረዳዎች ትርምስ ፈጥረዋል" ብሏል። የክልሉ መንግስት ከህዝቡ ጋር ተባብሮ ያመጣውን ሰላም እና ልማት ወደ ኋላ ለመመለስ እየሰሩ ያሉ እነዚህ በእኩይ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ሀይሎች በየቦታው ሰዎችን በመግደል፣ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት በማድረስ እና ህይወት እንዲጠፋ በማድረግ፣ የፀጥታ አካላትን እና አመራርን ኢላማ በማድረግ ወደ ለየለት የሕዝቦች እልቂት ለማስገባት የተለያዩ ሙከራዎችን እያደረጉ እንደሆነም ክልሉ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል። የክልሉ መንግሥት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ተጠርጣሪዎችን አድኖ በህግ ቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሆነም ተገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌደራል እና የክልሉ የፀጥታ አካላት አሁን ላይ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሰፊ ስራዎችን…
Read More
ኢትዮጵያ ሁሉንም የስፖርት ውርርድ ቤቶች ፈቃድ ሰረዘች

ኢትዮጵያ ሁሉንም የስፖርት ውርርድ ቤቶች ፈቃድ ሰረዘች

በኢትዮጵያ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሲሰሩ የቆዩ የሁሉም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ መሰረዙ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ሁሉንም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃዶች ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መሰረዛቸውን ገልጿል። የፈቃድ ስረዛው በውርርድ እና በፋይናንስ ዘርፉ ላይ በተካሄደ አገር አቀፍ ጥልቅ ግምገማ ላይ ተመስርቶ የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል። ውሳኔው በስራ ላይ ባሉትና ቀደም ሲል በይፋ በታገዱት በሁሉም የውርርድ ድርጅቶች በእኩልነት ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሂደት ላይ ያለው ምርመራ በዘርፉ ውስጥ የተንሰራፋ ሀገ-ወጥ አሰራር፣ የፈቃድ ውል ጥሰት እና ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሚሆኑ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውሮች እንዳሉ በግልጽ አመላክቷል። ለስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እና ሲስተም…
Read More
ኤርትራ ከኢጋድ ለመልቀቅ ያሳለፈችውን ውሳኔ ዳግም እንድታጤነው ተጠየቀች

ኤርትራ ከኢጋድ ለመልቀቅ ያሳለፈችውን ውሳኔ ዳግም እንድታጤነው ተጠየቀች

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ፤ የኤርትራ መንግሥት ከድርጅቱ የመውጣት ውሳኔ ያሳለፈው “ተጨባጭ ሃሳቦች ወይም በአይነተኛ ተቋማዊ ወይም የፖሊሲ ማሻሻያዎች ዙሪያ ተሳትፎ” ሳያቀርብ መሆኑን በማንሳት ቅሬታውን ገልጿል። ኢጋድ ይህንን ውሳኔ በይፋዊ የቃል ማስታወሻ መግባቱን አረጋግጧል። ሆኖም ግን፣ ሴክሬታሪያቱ ለድርጅቱ የተላከው ማስታወሻ ከማንኛውም ቀደም ያለ ውይይት ውጪ መሆኑን ጠቁሟል። ኤርትራ ለሁለት አሥርት ዓመታት ያህል በራሷ ፍላጎት አባልነቷን ካገደች በኋላ፣ እ.ኤ.አ. ሰኔ 2023 በተካሄደው 14ኛው የልዩ መሪዎች ጉባኤ ላይ በሁሉም አባል አገሮች በሞቃት አቀባበል ወደ ድርጅቱ ተመልሳ ነበር ብሏል። በዚያን ወቅት፣ መመለሷ “ሁሉን አቀፍነት፣ የክልላዊ ወንድማማችነት እና የታደሰ ትብብር የጋራ ቁርጠኝነት” ማሳያ እንደነበር ድርጅቱ አስታውሷል። ነገር ግን፣ ኢጋድ ከሰኔ 2023…
Read More
የቀድሞው ጉምቱ ባለስልጣን የ13 ዓመት እስር ተፈረደባቸው

የቀድሞው ጉምቱ ባለስልጣን የ13 ዓመት እስር ተፈረደባቸው

የቀድሞው የአደጋ ስጋት ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በሙስና ወንጀል በ13 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የቀድሞ ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ በከባድ የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በ50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል። የፍትሕ ሚኒስቴር ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ፣ አቶ ምትኩ ከሌሎች ተባባሪዎች ጋር በመሆን የተረጂዎችን ቁጥር በማጋነን ከ601 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴን ጨምሮ በርካታ የምግብ እርዳታ ቁሳቁሶችን ከመጋዘን በማውጣት ለተረጂዎች ሳይደርስ ለዱቄት ፋብሪካዎችና ለሌሎች በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉ አስረድቷል። በተጨማሪም፣ ከ472 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ በሕገ ወጥ መንገድ እንዲከፈል በማድረግ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ…
Read More