Simretparty

ስምረት ፓርቲ በትግራይ “አዲስ ሕዝባዊ የፖለቲካ ትግል” እንዲጀመር አሳሰበ

ስምረት ፓርቲ በትግራይ “አዲስ ሕዝባዊ የፖለቲካ ትግል” እንዲጀመር አሳሰበ

የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ስምረት (ስምረት)፣ በትግራይ ፖለቲካ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ህወሀት በሀይል ስልጣን መቆጣጠሩን አስታውቋል። በትግራይ ክልል ስልጣን በሀይል የተቆጣጠረው ሀይል ክልሉን ወደ ከፋ የጦርነት ድባብና “ሰው አልባ” መዋቅር እየመራው መሆኑንም አስታውቋል። ፓርቲው የድርጅቱ ምክር ቤት ከግንቦት 29 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ያካሄደውን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ማጠናቀቁን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፣ በትግራይ ክልል እየተባባሰ መጥቷል ያለው “የኋላ ቀር ቡድን” ውሳኔ የህልውና አደጋ እየደገነ መሆኑን አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት በክልሉ ውስጥ የወጣቶች እፈሳ፣ ከፍተኛ የስደት ፍሰት፣ የምሁራን መበተን እና ከባድ የኑሮ ውድነት መንገሱን ድርጅቱ በዝርዝር አስረድቷል።የስምረት ምክር ቤት በመግለጫው፣ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ሥልጣን ላይ ያለው “ኋላ ቀር ቡድን የኤርትራን መንግሥት የወታደራዊ…
Read More