Srilanka

በኢትዮጵያ የሚኖሩ የስሪላንካ ዜጎችን ያገቱ ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በኢትዮጵያ የሚኖሩ የስሪላንካ ዜጎችን ያገቱ ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በኢትዮጵያ የስሪላንካ ኤምባሲ ተወካይ ግንቦት 23/2026 ለስራ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሦስት ዜጎቹ እንደተሰወሩ እና ሲሪላንካ ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ተደውሎ እያንዳንዳቸው 30 ሺ ዶላር እንዲከፍሉ መጠየቃቸውን ግንቦት 26 ቀን 2026  በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ሪፖርት አደረጉ። በአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ ወንጀል ፈፃሚዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትልና የምርመራ ቡድን በማዋቀር ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ እንደገለጸው ከሌሎች የፀጥታ ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ባሰባሰበው መረጃ ሦስቱ ግለሰቦች በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C- 40463/AA በሆነች ሱዚኪ ዲዛየር  መኪና ከኤርፖርት ተሳፍረው መሄዳቸውን አረጋግጧል። የክትትል ቡድኑ አባላት አሽከርካሪውን  ጨምሮ 2 ኢትዮጵያውያንን እና 4 የፓኪስታን…
Read More