20
Jun
በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የታገቱትን ሰዎች ለማስለቀቅ ለእያንዳንዳቸው አንድ ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገብረ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ ባሳለፍነው ቅዳሜ ማለዳ ላይ ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር በመጓዝ ላይ የነበሩ ከ50 በላይ መንገደኞች ታይተዋል ። እገታውን የፈጸሙት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው የተባለ ሲሆን ለአንድ ሰው አንድ ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ የታጋች ቤተሰቦች ታጣቂዎቹ እየደወሉ መጠየቃቸው ተገልጿል። እገታው የተፈጸመበት ስፍራ ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ 75 ኪሎ ሜትር ላይ ሲሆን የፌደራል ፖሊስም ሆነ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ታጣቂዎቹ በዜጎች ላይ እገታውን ሲፈጽሙ ማስጣል እንዳልቻለ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል ። በዚህ አካባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የሚያደርሱትን ጥቃት በመፍራት የሌሊት ጉዞ ከቆመ አንድ ዓመት እንዳለፈውም ነዋሪዎቹ…