Rabis

በአዲስ አበባ ለ153 ሺህ ውሾች የእብድ ውሻ ክትባት መስጠት ተጀመረ

በአዲስ አበባ ለ153 ሺህ ውሾች የእብድ ውሻ ክትባት መስጠት ተጀመረ

የግብርና ሚኒስቴር እንደገለጸው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ "የእብድ ውሻ በሽታ" እየተባለ የሚጠራውን በንክሻ እና ቡጭሪያ ወደ ሰዎች የሚተላለፍ በሽታን ለማስቀረት ያለመ ክትባት በመሰጠት ላይ መሆኑን አስታውቋል። በሽታው በሰዎች ላይ እስከ ሞት የሚያደርስ አደጋ የሚያስከትል በመሆኑ "የውሻ እብደት"በሽታን ለመከላከል 150 ሺህ ውሾችን ለመከተብ ዕቅድ ይዞ እየሰራ እንደሆነም ሚንስቴሩ አስታውቋል። ከሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም የጀመረው ይህ ዘመቻ ለእንስሳቱ የቤት ለቤት ክትባት መስጠትን አላማ ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል። ሚኒስቴሩ ከዚህ ቀደም በሀገር አቀፍ ደረጃ ባከናወነው መደበኛ ክትባት ከ100 ሺህ በላይ ውሾችን የከተበ ሲሆን፤ ዘመቻው የውሻ እብደትን ከመከላከል ባለፈ የሰዎችን ደህንነት መጠበቅን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የእንስሳት ጤና መሪ ሥራ አስፈጻሚው ዶክተር ሲሳይ ጌታቸው ተናግረዋል።…
Read More