የተጣራ መረጃ

ኢትዮጵያ የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርትን ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርትን ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ ሂዩማን ራይትስ ዋች በትግራይ ክልል ተፈጸመ በሚል ያወጣውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርት እንደማትቀበለው አስታውቃለች። በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል የሰላም ስምምነት ቢፈረምም አሁንም በትግራይ ምዕራባዊ አካባቢዎች የሚካሄደው የዘር ማጽዳት ወንጀል መቀጠሉንና የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላትም ለፈጸሙት ግፍ ተጠያቂ አልተደረጉም በማለት ሂዩማን ራይት ወች ከሰሞኑ ያወጣውን ሪፖርት አስመልክቶ መንግስት ምላሽ ሰጥቷል፡፡ መንግስት በምላሹም ሪፖርቱ በአንዳንድ አካባቢዎች ጉልህ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚገልጽ መሰረተ ቢስ ሪፖርት ነው ሲል ተችቷል። አክሎም በሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል የነበረው ግጭት በርካታ አካባቢዎችን ለጉዳት ያጋለጠ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ የተወሰነ አካባቢን መርጦ ደጋግሞ ሪፖርት በማዘጋጀት በሰብዓዊ መብት አጀንዳ ሽፋን የተለየ የፖለቲካ ተልዕኮዉን ለማሳካት ዓላማ ያደረገ…
Read More
የጸጋ በላቸው ጠላፊ በቁጥጥር ሥር ዋለ

የጸጋ በላቸው ጠላፊ በቁጥጥር ሥር ዋለ

የዳሽን ባንክ ሐዋሳ ቅርንጫፍ ባልደረባ የሆነችውን ጸጋ በላቸው በማገት ወንጀል የተጠረጠረውና ክትትል ሲደረግበት የቆየው ዋና ሳጂን የኋላ መብራት በቁጥጥር ሥር መዋሉን የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፤ ግለሰቡ የጸጥታ ኃይሉ ባደረገው ክትትል፤ ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ላይ በሀገረ ሰላም ወረዳ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ገልጿል። የጸጥታ ኃይሉ ቀደም ሲል ተበዳይዋን ከጠላፊው ማስጣል መቻሉን ያስታወሰው የሰላምና ጸጥታ ቢሮው፤ በወቅቱ ያመለጠው ተጠርጣሪው ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን፤ በሻፋሞ ጫካ ለጫካ ሲዘዋወር እንደነበረ መቆየቱን ተገልጿል። በዚህም ተጠርጣሪው አካባቢ በመቀየር ፍለጋውን አስቸጋሪ ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን፤ ማህበረሰቡን በማሳተፍ በተደረገው አሰሳ በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተመላክቷል። ተጠርጣሪው ግለሰብ ወንጀሉን ለመፈጸም ሲጠቀምባቸው…
Read More
ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ

ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ

ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ የዓለማችን ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ እና ብዙ ህዝብ ያላቸው ሩሲያ እና ቻይና የኢትዮጵያ የስራ ቋንቋ የሆነው አማርኛ ቋንቋ ለዜጎቻቸው እንዲሰጥ መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ሩሲያ ከቀጣዩ መስከረም ወር ጀምሮ በሞስኮ በሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጻለች፡፡ ትምህርቱ ከቀጣዩ መስከረም 2016 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል የተባለ ሲሆን በሳምንት ሁለት ክፍለ ጊዜ እንደሚሰጥ በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የእስያ እና አፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ ገልጸዋል፡፡ ሌላኛዋ አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቿ ለማስተማር የወሰነችው ሀገር ቻይና ስትሆን ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) ከሚሰጡ 101 የውጭ ቋንቋ ትምህርቶች አንዱ ይሆናል ተብሏል፡፡ ለዚህ እንዲረዳም አማርኛን ለቻይናዊያን ተማሪዎች ለማስተማር የሚያግዘው መጽሀፍ በቤጂንግ…
Read More
በትግራይ ክልል ከ3500 በላይ መምህራንና ተማሪዎች መገደላቸው ተገለጸ

በትግራይ ክልል ከ3500 በላይ መምህራንና ተማሪዎች መገደላቸው ተገለጸ

የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ለሁለት ዓመታት በዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በትግራይ ክልል ስላደረሰው ውድመት ግንቦት መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የአስተዳደር በደል መከላከል ዳይሬክተር አዳነ በላይ በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ከ2ሺህ በላይ መምህራን እና ከ 1 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች መገደላቸው ተረጋግጧል ብለዋል። ተቋሙ በሰጠው መግለጫ በትግራይ ክልል ብቻ 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን በሁሉም የማበረሰብ ክፍል ላይ ጦርነቱ ውድመት ማድረሱ ተገልጿል። በዚሁ ጦርነት ምክንያት 88 በመቶ የመማሪያ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ እና በከፊል ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባለ ሲሆን 60 በመቶ የመማሪያ መፃሕፍት ደግሞ ከጥቅም ውጪ ሆነዋል ተብሏል። እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ የጦርነቱ ዳፋ መሠረተ ልማቶቹን በማውደም እና…
Read More
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት 28 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ማድረሱ ተገለጸ

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት 28 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ማድረሱ ተገለጸ

በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይም ማዕከሉን በትግራይ ክልል አድርጎ ለሁለት ዓመታት በተካሄደውና በሌሎች የተወሰኑ አካባቢዎች በነበረው ጦርነት፣ ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳትና ኪሳራ በአገር ላይ መድረሱን ገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ። የገንዘብ ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ ተቋማቸው በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተካሄደው ጦርነት የደረሰውን ጉዳትና የመልሶ ግንባታ ፍላጎት የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት (Damage and Needs Assessment) ማከናወኑን ገልጸዋል ። በጥናት ግኝቱ መሠረትም ያጋጠመው አጠቃላይ ጉዳትና የኢኮኖሚ ኪሳራ በአጠቃላይ 28 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን ተገልጿል። ለምክር ቤቱ በቀረበው ሪፖርት ላይ ከተቀመጠው መረጃ መረዳት እንደተቻለው፣ ‹‹22 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 20.4…
Read More
ህወሓት የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ሕልውናዬን የሚያከስም በመሆኑ አልቀበለውም አለ

ህወሓት የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ሕልውናዬን የሚያከስም በመሆኑ አልቀበለውም አለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሰሞኑ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጉዳይ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡ ቦርዱ ከዚህ በፊት ህወሓት ከምርጫ ቦርድ እውቅና ውጪ ምርጫ በማድረጉ፣ ወደ ትጥቅ ትግል እና አመጽ ተግባር ገብቷል በሚል ፓርቲው እንዲከስም ውሳኔ አስተላልፎ ነበር፡፡ ህወሓት ለምርጫ ቦርድ ባስገባው ማመልከቻ ጦርነቱ በሰላም ስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ እና ከሽብርተኝነት መሰረዙን ተከትሎ  በምርጫ ቦርድ የተላለፈብኝ ውሳኔ ይነሳልኝ ሲል አመልክቶ ነበር፡፡ ምርጫ ቦርድም ከዚህ በፊት በህወሓት ላይ ያስተላለፍኩት ውሳኔን መቀልበስ የምችልበት ህጋዊ አሰራር የለም ሲል ምላሽ ሰጥቶም ነበር፡፡ ይህንን ተከትሎም ህወሓት ከቀናት በፊት ምርጫ ቦርድ ያሳለፈውን ውሳኔ እንደማይቀበለው ባወጣው መግለጫ አሳውቋል። የምርጫ ቦርድን ውሳኔ " አልቀበለውም " ያለው ህወሓት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር…
Read More
በሰርግ ላይ በተተኮሰ ጥይት ሙሽራው እና አባትየው ተገደሉ

በሰርግ ላይ በተተኮሰ ጥይት ሙሽራው እና አባትየው ተገደሉ

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን በቋሪት ወረዳ ወይበኝ ቀበሌ ልዩ ቦታው በተለምዶ አነሳት እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ በተዘጋጀ ሰርግ ላይ የሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል። በባህሉ በወጉ መሰረት ልጃችንን ለልጃችሁ ተባብለው ሙሽሪትና ሙሽራው ሊጣመሩ የሙሽራው ቤተሰብና የሙሽሪት ቤተሰብ በስጋ ዝምድና ሊጣመሩ ቤት ባፈራው እንደአቅም ድግስ በመደገስ የሩቁና የቅርቡ ወዳጅ ዘመድ ልጃችንን ስለምንድር ልጃችንን መርቁልን ማለት የተለመደ ስርዓትና ወግ ነው፡፡ በትናንትናው ዕለት ማለትም ግንቦት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ለሰርጉ ድምቀት የተጠራው ወዳጅ ዘመድ በተሰበሰበበት ወደ ቤታቸው ሊወጡ ሲሉ የደስ ደስ ጥይት ይተኮሳል። በዚህ ሰዓትም በተተኮስ ጥይት ሙሽራው እና የሙሽራው አባት ወዲያውኑ ህይታቸው ማለፉ ተገልጿል። እንዲሁም አንድ የሴት ሚዜ አና ሰርጉን ለማድመቅ የተገኙ 4…
Read More
በአዲስ አበባ የአንድ ወረዳ ስራ አስፈጻሚ ተገደሉ

በአዲስ አበባ የአንድ ወረዳ ስራ አስፈጻሚ ተገደሉ

በአዲስ አበባ የአንድ ወረዳ ስራ አስፈጻሚ ተገደሉ በአዲስ አበባ ከተማ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አለባቸው አሞኜ በቢሮአቸው ውስጥ ተገደሉ። የክፍለ ከተማው ኮሚኒኬሽን ባሰራጨው መረጃ ፤ " አቶ አለባቸው አሞኜ ቢሯቸው ውስጥ ቁጭ ብለው የህዝብ አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት ከአንድ ተገልጋይ በሽጉጥ ተገድለዋል። ክፍለ ከተማው ስለ ግድያው ተጨማሪ መረጃ ባያደርግም ግድያውን ፈጽማል የተባለለው ተጠርጣሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል ብሏል። ክፍለከተማው ባወጣው መግለጫ " አቶ አለባቸው በስራ ቁርጠኝነት የሚታወቁ ናቸው" "በበርካታ መንግስታዊና ህዝባዊ ተግባራት አርዓያነት ያለው ስራ የሰሩና ያስተባበሩ አመራራችን ነበሩ " ሲል ገልጿል። አመራሩ በደረሰባቸው ጥቃት ወደ ህክምና ቦታ ቢወሰዱም ህይወታቸውን ማትረፍ እንዳልተቻለ ተገልጿል።
Read More
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፍሰት የሁለት ቢሊዮን ዶላር ጉድለት አሳየ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፍሰት የሁለት ቢሊዮን ዶላር ጉድለት አሳየ

ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ አቅዳ እንደነበር ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርቱ ላይ እንደገለጸው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር አግኝታለች፡፡ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ እንዳሉት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 4.5 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ወደ አገር ውስጥ ለመሳብ ታቅዶ 2.67 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡ የኮሚሽኑ አፈጻጸም የዕቅዱን 61 በመቶ ብቻ ያሳካ ሲሆን በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ጦርነት፣ በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ያለው አለመረጋጋት እንዲሁም በዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ምክንያት ያጋጠመው የዓለም ኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ለአፈጻጸሙ መቀነስ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል፡፡ ወደ…
Read More
ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን ሾመ

ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን ሾመ

ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳፋሪኮም ቴሌኮም ኩባንያ አዲስ ሀላፊ ሾሟል። ላለፉት ሶስት ዓመታት በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አዲስ ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል። አምባሳደር ሔኖክ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳዮች እና ቁጥጥር ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለኢትዮ ነጋሪ እንዳረጋገጠው አምባሳደር ሔኖክ የቀድሞውን የድርጅቱ መሪ የነበሩት ማቲው ሀሪሰንን ተክተዋል። አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ ከ2018 እስከ 2022 ድረስ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከ20 በላይ ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን በቅርቡም በኤምፔሳ አማካኝነት የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ እንደሚያገኝ ተገልጿል።
Read More